ዘኍል 31:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁለት መድባችሁም አንደኛውን ክፍል ወደ ጦርነት ለሄዱ ወታደሮች፥ ሁለተኛውን ክፍል ለቀሩት የማኅበሩ አባላት ስጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምርኮውንም ለሁለት ከፍላችሁ በጦርነቱ ለተካፈሉት ወታደሮችና ለቀረው ማኅበረ ሰብ አከፋፍሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምርኮውንም ወደ ጦርት ወጥተው በተዋጉትና፥ በማኅበሩም ሁሉ መካከል ለሁለት ክፈል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምርኮውንም በተዋጉትና ወደ ሰልፍ በወጡት፥ በማኅበሩም ሁሉ መካከል ትከፍላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምርኮውንም በተዋጉትና ወደ ሰልፍ በወጡት፥ በማኅበሩም ሁሉ መካከል አስተካክለህ ክፈል። |
እንዲህም አላቸው፤ “እነሆ፥ አሁን በምርኮ ያገኛችሁትን ብዙ ከብት፥ ብር፥ ወርቅ፥ ነሐስ፥ ብረትና ብዙ ልብሶች ይዛችሁ ወደ መኖሪያችሁ ልትመልሱ ስለ ሆነ ከጠላቶቻችሁ በምርኮ ያገኛችሁትን ምርኮ ከዘመዶቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”