ዘኍል 31:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ግን ከጦርነት በተመለሱት በጭፍራ አለቆች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም ከጦርነት በተመለሱት በሰራዊቱ አዛዦች፣ ማለትም በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጦሩ አዛዦች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጭፍራ አለቆች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጭፍራ አለቆች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ። |
ከዚህ በኋላ ያ ነቢይ ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘እኔ ይገደል’ ብዬ የፈረድኩበትን ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል፤ ”
ይህም ኤልሳዕን አስቈጣው፤ ስለዚህም ንጉሡን “አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መተህ ቢሆን ኖሮ በሶርያውያን ላይ ፍጹም ድልን ትቀዳጅ ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ድል ትነሣቸዋለህ” አለው።
ሙሴ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት በመሆን ቀርቦ የነበረውን ፍየል ምን እንዳደረጉት በጠየቀ ጊዜ ተቃጥሎ እንደ ነበር ተረዳ፤ ይህም ነገር በአልዓዛርና በኢታማር ላይ ሙሴን ስላስቈጣው እንዲህ ሲል ጠየቀ፥
ከእነርሱም አንዳንዶቹን የሺህ አለቆችና የኀምሳ አለቆች አድርጎ ይሾማል፤ ወንዶቹ ልጆቻችሁ የንጉሡ ሁዳድ አራሾችና መከር ሰብሳቢዎች ይሆናሉ፤ ሌሎችም የጦር መሣሪያና የሠረገላ ዕቃ ሠራተኞች ይሆናሉ።