ዘኍል 30:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባል ያላገባች ሴት አስባም ሆነ በግድየለሽነት ስእለት ካደረገች ወይም ከአንድ ነገር ለመከልከል ቃል ከገባች በኋላ ባል ብታገባ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲሁም ከተሳለች ወይም አምልጧት ተናግራ ራሷን ግዴታ ውስጥ ካስገባች በኋላ ባል ብታገባ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስእለትም ከተሳለች ወይም ራስዋን በመሐላ ያሰረችበትን ነገር ከአንደበትዋ በችኮላ ከተናገረች በኋላ ባል ብታገባ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ባል ያገባች ብትሆን፥ በአንደበቷም እንደ ተናገረች ስለ ራስዋ የተሳለችው ስእለት በራስዋ ላይ ቢሆን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተሳለችም ጊዜ ራስዋንም በመሐላ ያሰረችበት ነገር ከአፍዋ በወጣ ጊዜ ባል ያገባች ብትሆን፥ |
ሴቶችም ጨምረው ሲናገሩ፥ “በሰማይ ንግሥት እንጎቻ በምንጋግርበት ጊዜ፥ ለእርስዋ መሥዋዕትና የወይን ጠጅ መባ በምናቀርብበት ጊዜ፥ ከባሎቻችን ተለይተን ያደረግነው ነገር አልነበረም።”
“አንድ ሰው ለክፉም ሆነ ለደግ ስለ ምንም ነገር ያለ ጥንቃቄ በግዴለሽነት ስእለት ቢሳል፥ ያደረገውን ስሕተት ካወቀበት ጊዜ አንሥቶ በደል ይሆንበታል።
አባትዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ስእለትዋን እንዳትፈጽም የሚቃወማት ከሆነ ግን ስእለትዋን የመፈጸም ግዴታ አይኖርባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው አባትዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል።
ሐናም እንዲህ ስትል ስእለት ተሳለች፦ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እኔን አገልጋይህን ተመልከተኝ! መከራዬንም በማየት አስበኝ! አትርሳኝም! አንድ ወንድ ልጅ ብትሰጠኝ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የተለየ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ጠጒሩም ከቶ አይላጭም።”