1 ሳሙኤል 1:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ሐናም እንዲህ ስትል ስእለት ተሳለች፦ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እኔን አገልጋይህን ተመልከተኝ! መከራዬንም በማየት አስበኝ! አትርሳኝም! አንድ ወንድ ልጅ ብትሰጠኝ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የተለየ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ጠጒሩም ከቶ አይላጭም።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝና አገልጋይህን ሳትረሳት ወንድ ልጅ ብትሰጣት፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለአገልጋይህም ወንድ ልጅ ብትሰጣት፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለጌታ እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አያርፍም።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 እርስዋም፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ የባሪያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ እኔንም ባትረሳ፥ ለባሪያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ፥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፥ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም ብላ ስእለት ተሳለች። Ver Capítulo |