እንዲሁም እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና ቤተ መቅደሱን የመንከባከብ ኀላፊነት የእነርሱ ነበር፤ በተጨማሪም በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚፈጸመው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ዘመዶቻቸውን የአሮን ዘሮች የሆኑ ካህናትን ይረዱ ነበር።
ዘኍል 3:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመገናኛው ድንኳን የጌርሾን ልጆች ኀላፊነት የነበረው በመገናኛው ድንኳን፥ ከውጪና ከውስጥ በኩል ባለው መሸፈኛ፥ በመግቢያው ደጃፍ መጋረጃ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጌርሶናውያን ኀላፊነት በመገናኛው ድንኳን ማደሪያውንና ድንኳኑን፣ መደረቢያዎቹን እንዲሁም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያለውን መጋረጃ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌድሶናውያንም በመገናኛው ድንኳን የሚጠብቁት ማደሪያውን፥ ድንኳኑን፥ መደረቢያውን፥ የመገናኛውንም ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌድሶን ልጆች በምስክሩ ድንኳን የሚጠብቁት ማደሪያውና ድንኳኑ፥ መደረቢያውም፥ የምስክሩ ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌድሶናውያንም በመገናኛው ድንኳን የሚጠብቁት ማደሪያው፥ ድንኳኑም፥ መደረቢያውም፥ የመገናኛው ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥ |
እንዲሁም እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና ቤተ መቅደሱን የመንከባከብ ኀላፊነት የእነርሱ ነበር፤ በተጨማሪም በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚፈጸመው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ዘመዶቻቸውን የአሮን ዘሮች የሆኑ ካህናትን ይረዱ ነበር።
ንጉሥ ሕዝቅያስ የካህናትንና የሌዋውያንን ሥርዓት እንደገና አቋቋመ፤ በዚህም ጉባኤ ውስጥ እያንዳንዱ ካህንና እያንዳንዱ ሌዋዊ የተለየ የሥራ ምድብ ነበረው፤ ይህም የሥራ ምድብ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕትን ማቅረብን፥ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚከናወነው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት መሳተፍን፥ በሌሎቹም በቤተ መቅደሱ ልዩ ልዩ ክፍሎች ምስጋናና ውዳሴ ማቅረብን የሚያጠቃልል ነበር፤
በዚህ ፈንታ ሌዋውያንን በመገናኛው ድንኳንና በውስጡም ባሉት የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ኀላፊዎች አድርገህ መድባቸው፤ እነርሱ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ በድንኳኑም ውስጥ ያገለግላሉ፤ በዙሪያውም ይሰፍራሉ።
ይህም፥ ቤቱን ትቶ ወደ ሩቅ አገር የሄደውን ሰው ይመስላል፤ እርሱም እያንዳንዱን አገልጋይ በልዩ ልዩ የሥራ ኀላፊነት ላይ መደበ፤ ዘበኛውንም ተግቶ እንዲጠብቅ አዘዘው።
ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! ከዚህ ቀደም ስለ አንተ በትንቢት በተነገረው መሠረት የሚከተለውን ትእዛዝ በዐደራ እሰጥሃለሁ፤ ትንቢቱን በመከተል መልካም ጦርነትን ተዋጋ፤