ዘኍል 3:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮን አራት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በኲሩ ናዳብ ሲሆን የቀሩት አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሮን ልጆች የበኵሩ ስም ናዳብ፣ የሌሎቹም አብዩድ አልዓዛርና ኢታምር ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ የአሮን ልጆች ስሞች ናቸው፤ በኩሩ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሮን ልጆች ስም ይህ ነው፤ በኵሩ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሮን ልጆች ስም ይህ ነው፤ በኵሩ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር። |
ዓምራምም አሮንና ሙሴ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ማርያም ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ወለደ። አሮንም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆች ነበሩት።
“ወንድምህን አሮንንና ልጆቹን ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን ወደ አንተ አቅርብ፤ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝም ዘንድ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ለያቸው።
አሮን የነአሶን እኅት የሆነችውን የዓሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ፤ እርስዋም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ወንዶች ልጆች ወለደችለት።
ናዳብና አቢሁ የተባሉት ሁለቱ የአሮን ልጆች እያንዳንዳቸው ጥናቸውን ወስደው፥ የእሳት ፍም ጭረው ጨመሩበት፤ በእርሱም ላይ ዕጣን አድርገው ወደ እግዚአብሔር አቀረቡ፤ ያን ዐይነት እሳት ያቀርቡ ዘንድ እግዚአብሔር ስላላዘዛቸው፤ ያ እሳቱ የተቀደሰ አልነበረም፤
ሙሴም አሮንንና ከሞት የተረፉትን ሁለቱን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታማርን እንዲህ አላቸው፦ “ለእግዚአብሔር ከቀረበው የምግብ መባ የተረፈውን ወስዳችሁ እርሾ ያልነካው ቂጣ ጋግሩ፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ መባ ስለ ሆነ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት።