ዘኍል 29:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ሙሴ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ነገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤላውያን ነገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ጌታ እርሱን ያዘዘውን ሁሉ ነገራቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ለእስራኤል ልጆች እግዚአብሔር ለሙሴ ያዘዘውን ሁሉ ነገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ለእስራኤል ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ ነገራቸው። |
“በተወሰኑላችሁ በዓሎች እነዚህን ለጌታ ታቀርባላችሁ፤ ይህም ከስእለት ቊርባናችሁ፥ በፈቃዳችሁ ከምታቀርቡት መባ ሌላ የሚቃጠል መሥዋዕታችሁን፥ የእህል ቊርባናችሁን፥ የመጠጥ ቊርባናችሁንና የአንድነት ቊርባናችሁን ታቀርባላችሁ።”
እኔ የተቀበልኩትን በመጀመሪያ ደረጃ ያለውን ነገር ለእናንተ አስተላለፍኩላችሁ፤ ያስተላለፍኩላችሁም ነገር በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈው ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤
“እግዚአብሔር አምላኬ እንድነግራችሁ ያዘዘኝን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አስተምሬአችኋለሁ፤ እርስዋን ለመውረስ በምትገቡባት ምድር ስትኖሩ እነዚህን ትእዛዞች አክብሩ።