ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረቡትን እንስሶች በየቤተሰቡ ለተመደበው ሕዝብ አከፋፈሉ፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት በኦሪት ሕግ በተሰጠው መመሪያ መሠረት መሥዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ ነው፤ እንዲሁም በበሬዎቹ አደረጉ፤
ዘኍል 28:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምግብ ቊርባን አድርጋችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ይኸውም ነውር የሌለባቸው ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንከን የሌለባቸው ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ፤ ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፤ እነርሱም ነውር የሌለባቸው መሆናቸውን ተመልከቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእሳትም የተደረገውን ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከላሞች ሁለት በሬዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነውር የሌለባቸው ይሁኑላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእሳትም የተደረገውን ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፤ ነውር የሌለባቸው ይሁኑላችሁ። |
ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረቡትን እንስሶች በየቤተሰቡ ለተመደበው ሕዝብ አከፋፈሉ፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት በኦሪት ሕግ በተሰጠው መመሪያ መሠረት መሥዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ ነው፤ እንዲሁም በበሬዎቹ አደረጉ፤
ይኸውም ከቀንድ ከብቱ መካከል አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበትን ኰርማ መርጦ ያምጣ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለት ዘንድ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በኩል ያቅርበው።
ተገቢ የሆነውንም የእህል ቊርባን በወይራ ዘይት የተለወሰ ምርጥ ዱቄት አቅርቡ፤ ይኸውም ከእያንዳንዱ ኰርማ ጋር ሦስት ኪሎ ዱቄት፥ ከአውራው በግ ጋር ሁለት ኪሎ ዱቄት፥
ይህን ሁሉ መሥዋዕትና የመጠጥ መባ በቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቊርባን ጋር ተጨማሪ በማድረግ ታቀርባላችሁ፤ እንስሶቹም ነውር የሌለባቸው መሆናቸውን አረጋግጡ።
ምንም ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ።
ነገር ግን እንስሶቹ እንከን ቢገኝባቸው ይኸውም ሽባ ወይም ዕውር ቢሆኑ፥ ወይም ደግሞ የባሰ ነውር ቢኖርባቸው፥ እነርሱን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ።