እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።
ዘኍል 27:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ በትእዛዜ ላይ ዐምፃችሁ ነበር፤ መላው ማኅበር በመሪባ ውሃ ዘንድ ሳሉ በእኔ ላይ በዐመፁ ጊዜ የተቀደሰውን ኀይሌን በእነርሱ ፊት መግለጥ እምቢ ብላችኋል፤” (መሪባ በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ የሚገኝ ምንጭ ነው።) አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ማኅበረ ሰቡ በጺን ምድረ በዳ ባለው ውሃ አጠገብ ባመፁ ጊዜ እኔን በሕዝቡ ፊት ቅዱስ አድርጋችሁ ለማክበር ሁለታችሁም ትእዛዜን ስላልጠበቃችሁ ነው።” ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ የሚገኝ የመሪባ ውሃ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በጺን ምድረ በዳ ማኅበሩ በተገዳደረኝ ጊዜ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አልቀደሳችሁኝምና።” ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የመሪባ ውኃ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አላከበራችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የክርክር ውኃ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አልቀደሳችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የመሪባ ውኃ ነው። |
እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።
“አሮን ለእስራኤላውያን ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር አይገባም፤ እናንተ ሁለታችሁ በመሪባ ውሃ ዘንድ በትእዛዜ ላይ ስላመፃችሁ አሮን ይሞታል።
ከግብጽ አውጥታችሁ ምንም ነገር ወደማይበቅልበት ወደዚህ አስከፊ ምድር ለምን አመጣችሁን? በዚህ ስፍራ እህል፥ በለስ፥ ወይንና ሮማን አይገኝም፤ ሌላው ቀርቶ የሚጠጣ ውሃ እንኳ የለም!”