ዘኍል 26:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሮቤል ነገድ ተወላጆች ሐኖክ፥ ፋሉስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በሄኖኅ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤ በፈሉስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል በኩር ሮቤል፤ የሮቤልም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሄኖኅ የሄኖኀውያን ወገን፥ ከፈሉስ የፈሉሳውያን ወገን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል በኵር ሮቤል፤ የሮቤል ልጆች፤ ከሄኖኅ የሄኖኃውያን ወገን፤ ከፈሉስ የፈሉሳውያን ወገን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል በኵር ሮቤል፤ የሮቤል ልጆች፤ ከሄኖኅ የሄኖኀውያን ወገን፥ ከፈሉስ የፈሉሳውያን ወገን፥ |
ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው።
የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች ቀጥሎ የተመለከቱት ናቸው፤ (ሮቤል የአባቱን አልጋ ደፍሮ በማርከሱ የብኲርናውን መብት ስላጣ፥ ያ መብት ለዮሴፍ ተሰጥቶ ነበር፤
የያዕቆብ በኲር ልጅ ሮቤል፥ ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔጽሮንና ካርሚ የሚባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሮቤል ነገድ አባቶች ናቸው።
“እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኻያና ከኻያ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ቈጠሩ።” ከግብጽ ምድር የወጡትም እስራኤላውያን እነዚህ ነበሩ፦