ዘኍል 26:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ልጆች በየወገናቸው፥ ምናሴና ኤፍሬም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሴፍ ዘሮች በምናሴና በኤፍሬም በኩል ያሉት በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የዮሴፍ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ምናሴና ኤፍሬም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሴር ልጆች በየወገናቸው፤ ከኢያምን የኢያምናውያን ወገን፥ ከኢያሱ የኢያሱያውያን ወገን፥ ከበርያ የበርያውያን ወገን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍ ልጆች በየወገናቸው፤ ምናሴና ኤፍሬም። |
ያዕቆብ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “ልጄ ዮሴፍ እኔ እዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለት ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ናቸው፤ ኤፍሬምና ምናሴ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ይቈጠራሉ።
በስተ ምሥራቅ ያለው የምናሴ ነገድ እኩሌታ በስተ ሰሜን እስከ ባዓልሔርሞን፤ እስከ ሠኒርና እስከ ሔርሞን ተራራ በሚደርሰው በባሳን ግዛት ውስጥ ይኖሩ ነበር፤ የሕዝባቸውም ቊጥሩ እየበዛ ሄደ፤
የምናሴ ልጆች፥ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤
ምድራቸው ምርጥ በሆነ ነገር ሁሉ የተመላ ይሁን፤ በሚቃጠለው ቊጥቋጦ ውስጥ ከተገለጠው አምላክ ጸጋ ይብዛለት። ከወንድሞቹ መካከል ግንባር ቀደም ለሆነው ልዑል ለዮሴፍ ይደረግለት።
የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም በምድሪቱ ለመኖሪያቸው የሚሆኑ ከተሞችና ለከብቶቻቸው ማሰማሪያ የሚሆን መሬት በቀር የርስት ድርሻ አልተሰጣቸውም፤