ስለዚህ እግዚአብሔር ከዚያን ጠዋት ጀምሮ እስከ ወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ ቸነፈር አመጣ፤ በሀገሪቱ ዳር እስከ ዳር ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺህ እስራኤላውያን አለቁ።
ዘኍል 25:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እስከዚያው ሰዓት ድረስ ያ መቅሠፍት ኻያ አራት ሺህ ሕዝብ አጥፍቶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም በመቅሠፍቱ የሞተው ሰው ቍጥር ሃያ አራት ሺሕ ደርሶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅሠፍትም የሞተው ሰው ሀያ አራት ሺህ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመቅሠፍቱም የሞቱት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅሠፍትም የሞተው ሀያ አራት ሺህ ነበረ። |
ስለዚህ እግዚአብሔር ከዚያን ጠዋት ጀምሮ እስከ ወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ ቸነፈር አመጣ፤ በሀገሪቱ ዳር እስከ ዳር ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺህ እስራኤላውያን አለቁ።
በፔዖር ሳለን የበለዓምን ምክር ተቀብለው ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት እንዲተዉ ያደረጉ ሴቶች መሆናቸውን ዘነጋችሁን? በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የአባር ቸነፈር መቅሠፍት ያመጣም ያ ስሕተት ነበር።
ከእነርሱ አንዳንዶቹ የዝሙት ኃጢአት እንደ ሠሩ እኛም የዝሙት ኃጢአት እንሥራ፤ እነርሱ ይህን በማድረጋቸው ከእነርሱ ኻያ ሦስት ሺህ ሰዎች በአንድ ቀን ሞተዋል።