‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
ዘኍል 24:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከያዕቆብ አንድ ገዢ ይወጣል፤ በከተማም ውስጥ የተረፉትን ጠራርጎ ያጠፋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገዥ ከያዕቆብ ይወጣል፤ የተረፉትንም የከተማዪቱን ነዋሪዎች ይደመስሳል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከያዕቆብም የሚወጣ ገዥ ይሆናል፥ ከከተማውም በሕይወት የተረፉትን ያጠፋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከያዕቆብም ኀያል ሰው ይወጣል፤ ከከተማውም የቀሩትን ያጠፋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከያዕቆብም የሚወጣ ገዥ ይሆናል፥ ከከተማውም የቀሩትን ያጠፋል። |
‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በኤፍራታ ምድር የምትገኚ ቤተልሔም ሆይ! ከይሁዳ ትናንሽ ከተሞች አንድ ብትሆኚም እንኳ ከአንቺ አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ የእስራኤልን ሕዝብ የሚመራ ገዢ ይወጣልኛል።”
እርሱ በእግዚአብሔር ኀይል ተነሥቶ የበግ መንጋውን ያሰማራል፤ ይህንንም የሚያደርገው በግርማዊው በእግዚአብሔር በአምላኩ ስም ነው፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ስለሚሆን እነርሱ ያለ ስጋት ይኖራሉ።
ከዚህ በኋላ በለዓም ወደ ዐማሌቅ በመመልከት እንዲህ ሲል ይህን የትንቢት ቃል ተናገረ፦ “ዐማሌቅ ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል ሕዝብ ነበረ፤ በመጨረሻ ግን እርሱ ራሱ ለዘለዓለም ይጠፋል።”