ኢዮርብዓም በኰረብቶች ላይ በሚገኙ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎች የሚያገለግሉ፥ ለአጋንንትና እርሱ ራሱ በጥጆች አምሳል ለሠራቸው ጣዖቶች የሚሰግዱ የራሱን ካህናት ሾሞ ነበር፤
ዘኍል 22:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ጠዋት ባላቅ በለዓምን የእስራኤልን ሕዝብ በከፊል ለማየት ወደሚቻልበት ወደ ባሞትበዓል አወጣው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት ባላቅ በለዓምን ወደ ባሞትባኣል አወጣው፤ እዚያም ሆኖ ሕዝቡን በከፊል አየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም ጠዋት ባላቅ በለዓምን ይዞ ወደ ባሞት-በኣል አወጣው፤ በዚያም ሆኖ ዳር ላይ የሰፈረውን ሕዝብ አየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም ባላቅ በለዓምን ይዞ ወደ በአል ኮረብታ አወጣው፤ በዚያም ሆኖ የሕዝቡን አንድ ወገን አሳየው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም ባላቅ በለዓምን ይዞ ወደ በኣል ኮረብታ መስገጃ አወጣው፤ በዚያም ሆኖ የሕዝቡን ዳርቻ አየ። |
ኢዮርብዓም በኰረብቶች ላይ በሚገኙ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎች የሚያገለግሉ፥ ለአጋንንትና እርሱ ራሱ በጥጆች አምሳል ለሠራቸው ጣዖቶች የሚሰግዱ የራሱን ካህናት ሾሞ ነበር፤
ልጆቻቸውንም መሥዋዕት አድርገው በእሳት ለማቃጠል ለባዓል መሠዊያዎችን ሠርተዋል፤ ይህን እንዲያደርጉ አላዘዝኳቸውም፤ ከቶም ስለዚህ ነገር አላሰብኩም።
ባላቅም በለዓምን “ከእስራኤላውያን ሁሉን ሳይሆን ጥቂቱን ብቻ ወደምታይበት ወደ ሌላ ቦታ ከእኔ ጋር እንሂድ፤ በዚያ ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ” አለው።