ዘኍል 21:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ያዕዜርን የሚሰልሉ ሰዎች ላከ፤ እስራኤላውያንም ከተማይቱንና በዙሪያዋ ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ያዙ፤ በዚያም ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያን አባረሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ሰላዮችን ወደ ኢያዜር ከላከ በኋላ እስራኤላውያን በአካባቢዋ ያሉትን መንደሮች በመያዝ እዚያ የነበሩትን አሞራውያን አባረሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ኢያዜርን እንዲሰልሉ ሰላዮችን ላከ፤ መንደሮችዋንም ወሰዱ፥ በዚያም የነበሩትን አሞራውያን አባረሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ሰላዮቹን ወደ ኢያዜር ላከ፤ እርስዋንና መንደሮችዋንም ያዙ፤ በዚያም የነበሩትን አሞሬዎናውያንን አባረሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ሰላዮችን ወደ ኢያዜር ሰደደ፤ መንደሮችዋንም ወሰዱ፥ በዚያም የነበሩትን አሞራውያን አባረሩ። |
ዮርዳኖስንም ተሻግረው በጋድ ውስጥ በሚገኘው ሸለቆ መካከል ባለችው በዓሮዔር ከተማ በስተ ደቡብ ሰፈሩ፤ ከዚያም ወደ ሰሜን አምርተው ወደ ያዕዜር ደረሱ፤
ለያዕዜር ሕዝብ ከማለቅሰው ይበልጥ ለሲብማ ሕዝብ እየጮኽኩ አለቅሳለሁ፤ የሲብማ ከተማ ሆይ! እንቺ ቅርንጫፎችዋ ሙት ባሕርን አልፎ እስከ ያዜር እንደሚደርስ የወይን ተክል ነሽ፤ ነገር ግን በጐመራው ፍሬሽና በወይን ዘለላሽ ላይ አጥፊው መጥቷል።
“ይህ እስራኤላውያን እንዲወርሱት እግዚአብሔር የረዳቸው የዐጣሮት፥ የዲቦን፥ የያዕዜር፥ የኒምራ፥ የሐሴቦን፥ የኤልዓሌ፥ የሲብማ፥ የነቦና የበዖን ከተሞች የሚገኙበት ምድር ለከብት ተስማሚ ነው፥ እኛ ደግሞ ብዙ ከብት አለን፤”
የእነርሱም ግዛት ያዕዜርንና በገለዓድ የሚገኙትን ከተሞች ሁሉ የዐሞንን ምድር እኩሌታ ጨምሮ ከራባ በስተምሥራቅ እስከምትገኘው እስከ ዓሮዔር ይደርሳል።
በሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት ላይ እንዳደረግሁት አስቀድሜ ከፊታችሁ ያባረራቸውን ተርብ ሰደድኩባቸው፤ ይህ በእናንተ ሰይፍ ወይም በእናንተ ቀስት የሆነ አይደለም።