ዘኍል 20:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ ውጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ወደ ሖር ተራራ ይዘሃቸው ውጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ ላይ አምጣቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ በማኅበሩ ሁሉ ፊት ወደ ሖር ተራራ ላይ አምጣቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ ላይ አምጣቸው፤ |
ከዚህ በኋላ ሙሴ አሮንን፥ እንዲሁም አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ሁለቱን የአሮንን ልጆች እንዲህ አላቸው፤ “ለሐዘን ብላችሁ ጠጒራችሁን አትላጩ፤ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ይህን ብታደርጉ ግን ትሞታላችሁ፤ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ቊጣውን ያወርዳል፤ ነገር ግን ወንድሞቻችሁ እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር በተላከ እሳት ስለሞቱት ልጆች እንዲያለቅሱ ተፈቅዶላቸዋል።
ነገር ግን ከእነርሱ ውስጥ ናዳብና አቢሁ በሲና በረሓ በእግዚአብሔር ፊት ያልተቀደሰ እሳት ጭረው በማቅረባቸው ተቀሥፈው ሞቱ፤ እነርሱም ልጆች አልነበሩአቸውም፤ ስለዚህም አልዓዛርና ኢታማር ብቻ አባታቸው አሮን በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ በክህነት ያገለግሉ ነበር።
(እስራኤላውያንም ከቤን ያዕቃን የውሃ ጒድጓዶች ተነሥተው ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ አሮንም በዚያው ሞቶ ተቀበረ፤ በእርሱም ምትክ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ።