“እነሆ አሁን የዐሞን፥ የሞአብና የኤዶም ሕዝቦችን ተመልከት፤ አደጋ ጥለውብናል፤ የቀድሞ አባቶቻችን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ወደነዚህ ሕዝቦች ግዛቶች እንዲገቡ አልፈቀድክላቸውም፤ የቀድሞ አባቶቻችን እነርሱን ዞረው አለፉ እንጂ አላጠፉአቸውም፤
ዘኍል 20:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በምድርህ አልፈን እንድንሄድ እባክህ ፍቀድልን፤ እኛም ሆንን ከብቶቻችን ከመንገድ ውጪ አንወጣም፤ ወደ እርሻዎችህም ሆነ ወደ ወይን ተክሎችህ አንገባም፤ ከውሃ ጒድጓዶችህም አንጠጣም፤ ግዛትህን እስክናልፍ ድረስ ከዋናው መንገድ አንወጣም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በአገርህ እንድናልፍ እባክህን ፍቀድልን፤ በየትኛውም ዕርሻ ወይም የወይን ተክል ውስጥ አንገባም፤ ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። የንጉሡን አውራ ጐዳና ይዘን ከመጓዝ በቀር፣ ግዛትህን ዐልፈን እስክንሄድ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፥ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፥ ከጉድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጐዳና እንሄዳለን፥ ግዛትህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፤ ከጕድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጎዳና እንሄዳለን፤ ዳርቻህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፥ ከጕድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጐዳና እንሄዳለን፥ ዳርቻህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም። |
“እነሆ አሁን የዐሞን፥ የሞአብና የኤዶም ሕዝቦችን ተመልከት፤ አደጋ ጥለውብናል፤ የቀድሞ አባቶቻችን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ወደነዚህ ሕዝቦች ግዛቶች እንዲገቡ አልፈቀድክላቸውም፤ የቀድሞ አባቶቻችን እነርሱን ዞረው አለፉ እንጂ አላጠፉአቸውም፤
መኖሪያው ኔጌብ የነበረ የከነዓናውያን ንጉሥ ዐራድ እስራኤላውያን በአታሪም በኩል መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በእነርሱ ላይ አደጋ ጥሎ ጥቂቶቹን ማረከ።
በኤዶም የሚኖሩ የዔሳው ዘሮችና በዔር የሚኖሩ የሞአብ ዘሮች በግዛታቸው በኩል እንድናልፍ እንደ ፈቀዱልን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረን እግዚአብሔር ወደሚያወርሰን ምድር እስክንገባ ድረስ በዚያ ለማለፍ ፍቀድልን።’