ንጉሥ ዖዝያ መንግሥቱን ባጠናከረ ጊዜ ዕብሪተኛ ሆነ፤ ይህም ዕብሪተኛነቱ ወደ ውድቀት አደረሰው፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ቤተ መቅደስ በድፍረት በመግባቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፤
ዘኍል 17:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ እኔ ለክህነት የምመርጠው ሰው በትሩ በማቈጥቈጥ ትለመልማለች፤ በዚህም ዐይነት እነዚህ እስራኤላውያን በየጊዜው በአንተ ላይ ማጒረምረማቸውን እንዲያቆሙ አደርጋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ የምመርጠው ሰው በትርም ታቈጠቍጣለች፤ እስራኤላውያን በእናንተ ላይ ነጋ ጠባ የሚያደርጉትንም ማጕረምረም በዚህ እገታለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ታቈጠቁጣለች፥ በእናንተም ላይ ያጉረመረሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጉረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ትለመልማለች፤ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁ የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ታቈጠቍጣለች፥ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁን የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ። |
ንጉሥ ዖዝያ መንግሥቱን ባጠናከረ ጊዜ ዕብሪተኛ ሆነ፤ ይህም ዕብሪተኛነቱ ወደ ውድቀት አደረሰው፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ቤተ መቅደስ በድፍረት በመግባቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዓለምን ስለ ክፋቱ፥ ክፉዎችን ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የኲራተኞችን ማን አለብኝነት አዋርዳለሁ፤ የትዕቢተኛውንም ጭካኔ አጠፋለሁ።
የእስራኤል ቅዱስ የሠራዊት አምላክ ያዘዘውን ሕግና ያስተማረውን ሥርዓት ስለ አቃለሉ ገለባና ድርቆሽ በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ የእነርሱም ሥር መሠረት በስብሶ ይጠፋል፤ አበባቸውም ደርቆ እንደ ትቢያ ይበናል።
ቤቶችሽን በእሳት ያቃጥላሉ፤ በብዙ ሴቶች ፊት ፍርድን ተግባራዊ ያደርጉብሻል፤ በዚህ ዐይነት አመንዝራነትሽንና ለወዳጆችሽ የዝሙት ዋጋ መክፈልሽን እንድትተዪ አደርግሻለሁ።
የዝሙት ሥራሽንና ገና በግብጽ ሳለሽ ጀምሮ የምትፈጽሚያቸውን አሳፋሪ ድርጊቶች ሁሉ እንድትተይ አደርጋለሁ፤ ዳግመኛም ወደ ጣዖቶች አትመለከቺም፤ ስለ ግብጽም አታስቢም።”
ሰፈራችሁን ለቃችሁ በምትሄዱበት ጊዜ ሌዋውያን ብቻ ድንኳኑን ነቅለው በሚሰፍሩበት አዲስ ቦታ ይተክሉታል፤ ከእነርሱ በቀር ወደ ድንኳኑ የሚቀርብ ማንኛውም ሰው በሞት ይቀጣል።
እስራኤላውያን ስለ ደረሰባቸው ችግር ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ እግዚአብሔርም የማጒረምረም ጩኸታቸውን ሰምቶ እጅግ በመቈጣት የሚባላ እሳት ላከባቸው፤ ያም እሳት ከሰፈሩ አንዱን ክፍል አወደመ።
ቆሬንና ተከታዮቹን እንዲህ አላቸው፦ “ነገ ጠዋት እግዚአብሔር ለእርሱ የተለየ ማን እንደ ሆነ ለይቶ ያሳየናል፤ ይኸውም የእርሱ የሆነውንና የመረጠውን በመሠዊያው ላይ ያገለግለው ዘንድ ወደ እርሱ እንዲቀርብ ይፈቅድለታል።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት መልሰህ አኑረው፤ ዐመፀኞች የሆኑ እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ካልተዉ እንደሚሞቱ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ይቀመጥ።”
ስለዚህ ሙሴ ይህንኑ ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ እያንዳንዱም መሪ በትሩን አምጥቶ ሰጠው፤ ስለያንዳንዱ የነገድ መሪ የሚሰጠው አንዳንድ በትር ሆኖ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት በትሮች ቀረቡ፤ ከእነዚያም በትሮች መካከል የአሮን በትር ነበረች፤
በማግስቱ ሙሴ ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ በሌዊ ነገድ ስም የቀረበችው የአሮን በትር ለምልማ አገኛት፤ ይኸውም እንቡጥ አውጥታ በማበብ የበሰለ የለውዝ ፍሬ አፍርታ ነበር።
እናንተም እንዲህ ብላችሁ ትነግሩአቸዋላችሁ፦ ‘የአምላካችሁ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በሚሻገርበት ጊዜ፥ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ መውረዱን አቆመ፤ ስለዚህም እነዚህ ድንጋዮች በዚህ ስፍራ የተደረገውን ሁሉ ለዘለቄታው ለእስራኤል ሕዝብ የሚያስታውሱ መታሰቢያዎች ናቸው።’ ”