ዘኍል 17:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት መልሰህ አኑረው፤ ዐመፀኞች የሆኑ እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ካልተዉ እንደሚሞቱ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ይቀመጥ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአሮን በትር ለዐመፀኞቹ ምልክት እንድትሆን መልሰህ በምስክሩ ፊት ለፊት አኑራት፤ እነርሱ እንዳይሞቱም በእኔ ላይ የሚያደርጉትን ማጕረምረም ይህ ይገታዋል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልሰህ አኑር፤ እርሱም ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆኖ ይቀመጥ፤ እነርሱም እንዳይሞቱ በእኔ ላይ ማጉረምረማቸውን ታስቆምበታለህ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ፥ እነርሱም እንዳይሞቱ ለማይሰሙ ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ ዘንድ የአሮንን በትር በምስክሩ ፊት አኑር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልስ፤ ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ እነርሱም እንዳይሞቱ ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ አለው። |
ሙሴም “እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው፤ ከግብጽ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ያዩ ዘንድ ከእርሱ አንድ አንድ ኪሎ ተኩል ሙሉ ለልጅ ልጆቻችሁ ይጠበቅ።” አለ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ በጊብዓ ኃጢአት ከሠሩበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ከማሳዘን አልተቈጠቡም፤ ስለዚህ በገባዖን ጦርነት ይነሣባቸዋል።
ጥናዎቹም የተቀደሱት ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ በቀረቡ ጊዜ ነው፤ ስለዚህ በኃጢአታቸው የተገደሉትን የእነዚህን ሰዎች ጥናዎች ውሰድና በመቀጥቀጥ እንዲሳሱ አድርግ፤ ለመሠዊያውም መክደኛ እንዲሆኑ አድርገህ ሥራቸው፤ ለእስራኤል ሕዝብ የመቀጣጫ ማስጠንቀቂያ ይሆናል።”
ይህም ሁኔታ የአሮን ዘር ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር ዕጣን ያጥን ዘንድ ወደ መሠዊያው መቅረብ እንደማይገባው ለእስራኤላውያን ሁሉ ማስጠንቀቂያ ይሆናል፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዲህ የሚያደርግ ሰው ሁሉ እንደ ቆሬና እንደ ተከታዮቹ ይጠፋል፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር።
“እግዚአብሔር አምላክህን በበረሓ እንዴት እንዳስቈጣኸው ከቶ አትርሳ፤ የግብጽን ምድር ለቀህ ከወጣህበት ቀን ጀምሮ እዚህ እስከ መጣህበት እስከ አሁን ድረስ በእርሱ ላይ ዐምፀሃል።
በዚህችኛዋ ክፍል ውስጥ የወርቅ ማዕጠንትና በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት ነበሩባት፤ ከዚህችም የኪዳን ታቦት ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብ፥ ለምልማ የነበረችው የአሮን በትር፥ ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባት ጽላት ነበሩ።
ነገር ግን ከዳዊት ጋር አብረው ከሄዱት መካከል የብልግና ጠባይ ያለባቸው አንዳንድ የማይረቡ ሰዎች “ከእኛ ጋር ወደ ጦርነቱ ስላልሄዱ ምርኮ ልናካፍላቸው አይገባም፤ ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ብቻ ተረክበው ወዲያ ይሂዱ” አሉ።