ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
ዘኍል 14:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐማሌቃውያንንና ከነዓናውያንን ፊት ለፊት ባያችሁ ጊዜ በጦርነት ትሞታላችሁ፤ እርሱን መከተል እምቢ ስላላችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በዚያ ያጋጥሟችኋልና። እግዚአብሔርን ስለ ተዋችሁትና እርሱም ከእናንተ ጋራ ስለማይሆን በሰይፍ ትወድቃላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በፊታችሁ ናቸውና በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ ጌታን ከመከተል ተመልሳችኋልና ጌታ ከእናንተ ጋር አይሆንም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐማሌቃዊና ከነዓናዊ በፊታችሁ ናቸውና በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ እግዚአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋልና እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አማሌቃዊና ከነዓናዊ በፊታችሁ ናቸውና በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ እግዚአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋልና እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም። |
ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
ዐዛርያስም ከንጉሥ አሳ ጋር ለመገናኘት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አሳ ሆይ! አድምጠኝ! እናንተም የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ ሆናችሁ ድረስ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ከፈለጋችሁትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፤
ዐማሌቃውያን በኔጌብ ምድር የሚኖሩ ሲሆን፥ ሒታውያን፥ ኢያቡሳውያንና አሞራውያን በተራራማው አገር፥ ከነዓናውያን ደግሞ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርና በሜዲቴራኒያን በባሕር ዳር ይኖራሉ።”
“እግዚአብሔር ለጠላቶችህ በአንተ ላይ ድልን ይሰጣቸዋል፤ በአንድ በኩል ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለማምለጥ በሰባት አቅጣጫ ትሸሻለህ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የሚደርሰውን ነገር በሚያዩበት ጊዜ በፍርሃት ይሸበራሉ፤
እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን መቋቋም ያልቻሉበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እነርሱ ራሳቸው እንዲጠፉ ስለ ተፈረደባቸው ከጠላቶች ፊት ወደ ኋላ ይሸሻሉ። እንዲደመሰስ የታዘዘውን ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ እኔ ከእናንተ ጋር አልሆንም።
ከዚያም በኋላ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው፤ እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ “እንደ ወትሮው በጣጥሼ እሄዳለሁ” ብሎ አሰበ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተለየው አላወቀም ነበር፤