የሁሉም ዕድል ፈንታው አንድ ዐይነት ነው፤ ይህም በዓለም እንደሚደረገው እንደማንኛውም ነገር ሁሉ እጅግ የከፋ ነው፤ ሰዎችም በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ አእምሮአቸው በክፋትና በእብደት የተሞላ ሆኖ በመጨረሻ ይሞታሉ።
ዘኍል 14:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ጠዋት ማልደው ተራራማይቱን አገር ለመውረር ተነሡ፤ እንዲህም አሉ፦ “እነሆ፥ እግዚአብሔር ሊያስገባን ወደነገረን ስፍራ ለመሄድ ተዘጋጅተናል፤ ኃጢአት መሥራታችንን ተገንዝበናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት ማልደው ወደ ተራራማው አገር ወጡ፤ እንዲህም አሉ፣ “ኀጢአት ሠርተናል፤ እግዚአብሔር ተስፋ ወደ ሰጠን ስፍራ እንወጣለን”። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም ማልደው ተነሡ፥ ወደ ተራራውም ራስ እንዲህ እያሉ ወጡ፦ እነሆ፥ እኛ በዚህ አለን፤ እኛ ኃጢአትን ሠርተናልና ጌታ ወዳለው ስፍራ እንወጣለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም ማልደው ተነሡ፤ ወደ ተራራውም ራስ ወጥተው፥ “እነሆ፥ እኛ ከዚህ አለን፤ በድለናልና እግዚአብሔር ወዳለው ስፍራ እንወጣለን” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም ማልደው ተነሡ፥ ወደ ተራራውም ራስ ወጥተው፦ እነሆ፥ መጣን፤ እኛ በድለናልና እግዚአብሔር ወዳለው ስፍራ እንወጣለን አሉ። |
የሁሉም ዕድል ፈንታው አንድ ዐይነት ነው፤ ይህም በዓለም እንደሚደረገው እንደማንኛውም ነገር ሁሉ እጅግ የከፋ ነው፤ ሰዎችም በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ አእምሮአቸው በክፋትና በእብደት የተሞላ ሆኖ በመጨረሻ ይሞታሉ።
በለዓምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በእርግጥ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ አንተ እኔን ለመቃወም በመንገድ ላይ መቆምህን አላወቅሁም ነበር፤ አሁንም ወደዚያ መሄዴ ስሕተት መስሎ ከታየህ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ።”
የቤቱ ጌታ ተነሥቶ በሩን ይዘጋዋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ በሩን በማንኳኳት፥ ‘ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ ማለት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም!’ ሲል ይመልስላችኋል።
“እናንተም ‘ሙሴ ሆይ፥ እኛ እግዚአብሔርን በድለናል፤ አሁን ግን አምላካችን እግዚአብሔር ባዘዘን መሠረት እንዋጋለን’ ብላችሁ መለሳችሁ፤ ኮረብታማይቱን አገር መውረር ቀላል መስሎአችሁ ከእናንተ እያንዳንዱ ለውጊያ ተዘጋጀ።
እግዚአብሔር ያለኝንም ለእናንተ ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን እምቢተኞች ሆናችሁ፤ በእርሱም ላይ ዐምፃችሁ በትዕቢታችሁ ብዛት ወደ ኮረብታማይቱ አገር ዘመታችሁ፤