ዘኍል 14:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እርስ በርሳቸው “ኑ! መሪ የሚሆነን ሰው መርጠን ወደ ግብጽ እንመለስ!” ተባባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳቸውም፣ “አለቃ መርጠን ወደ ግብጽ እንመለስ” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርስ በርሳቸውም፦ “ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብጽ እንመለስ” ተባባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብፅ እንመለስ” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስ በርሳቸውም፦ ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብፅ እንመለስ ተባባሉ። |
እስኪያንገፈግፋችሁና በአፍንጫችሁ እስኪወጣ ድረስ አንድ ወር ሙሉ ትመገቡታላችሁ፤ ይህም የሚሆነው እዚህ በመካከላችሁ ያለውን ጌታ ስለ ናቃችሁና፦ ከግብጽ ባልወጣን ኖሮ መልካም ነበር በማለት ስላለቀሳችሁ ነው።’ ”
ያም ንጉሥ ለሠራዊቱ ብዙ ፈረሶች ያሉት መሆን የለበትም፤ እግዚአብሔር ሕዝቡ ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ስለ አዘዘ ፈረሶችን ለመግዛት ወደ እዚያ ሰዎችን አይላክ።
እግዚአብሔር ‘ዳግመኛ ተመልሰህ ወደዚያ አትሄድም’ ብሎ የተናገረ ቢሆንም እንኳ በመርከብ ተሳፍረህ ወደ ግብጽ እንድትመለስ ያደርጋል፤ በዚያም ራስህን ለጠላቶችህ ባሪያ አድርገህ መሸጥ ትፈልጋለህ፤ ነገር ግን ባሪያ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልግህ እንኳ አታገኝም።”