La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 11:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሚበሉት ሥጋ ገና በብዛት ሳለ፥ እግዚአብሔር በሕዝቡ እጅግ ተቈጣ፤ ብርቱ መቅሠፍትም በሕዝቡ መካከል አመጣ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ሥጋው ገና በጥርስና በጥርሳቸው መካከል ሳለ አላምጠው ሳይውጡት የእግዚአብሔር ቍጣ በላያቸው ነደደ፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ መቅሠፍት ክፉኛ መታ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሥጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳይታኘክ የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ ጌታም ሕዝቡን እጅግ ታላቅ በሆነ መቅሠፍት መታ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሥጋ​ውም ገና በጥ​ር​ሳ​ቸው መካ​ከል ሳለ ሳያ​ኝ​ኩ​ትም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን እጅግ ታላቅ በሆነ መቅ​ሠ​ፍት አጠ​ፋ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሥጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳያኝኩትም፥ የእግዚአብሔር ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ መቅሠፍት እጅግ መታ።

Ver Capítulo



ዘኍል 11:33
10 Referencias Cruzadas  

እንዳያልቅበትም በአፉ ይዞ እያላመጠ ቢያቈየውም፥


በልቼ እጠግባለሁ ሲል እግዚአብሔር ኀይለኛ ቊጣውን ያወርድበታል። መዓቱንም በእርሱ ላይ ያዘንብበታል።


የምሥራቅ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፤ በኀይሉም የደቡብን ነፋስ አንቀሳቀሰ።


ስለዚህ ሕዝቡ በልተው ጠገቡ፤ እግዚአብሔር የተመኙትን ሁሉ ሰጣቸው።


በዚያን ጊዜ የሞቱት ሰዎች ቊጥር ከቆሬ ጋር ዐምፀው ያለቁትን ሳይጨምር ዐሥራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ነበር፤


ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ።


ነገር ግን እስከዚያው ሰዓት ድረስ ያ መቅሠፍት ኻያ አራት ሺህ ሕዝብ አጥፍቶ ነበር።


እግዚአብሔር ልትድን በማትችልበት በግብጻውያን የእባጭ በሽታ፥ በኀይለኛ የጨጓራ በሽታ፥ በቊስልና በሚያሳክክ በሽታ ይመታሃል፤