ዘኍል 10:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቃል ኪዳኑ ታቦት በተንቀሳቀሰ ጊዜ ሁሉ ሙሴ “እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ሁሉ ከፊትህ ይባረሩ!” ይል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታቦቱ ለጕዞ በተነሣ ጊዜ ሁሉ ሙሴ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ! ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ” ይል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባረፈም ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ወደ እስራኤል እልፍ አእላፋት ተመለስ” ይል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ ይል ነበር። |
እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።
ከጦርነት የተረፉት ወደ ሰፈራቸው በተመለሱ ጊዜ የእስራኤል መሪዎች እንዲህ አሉ፤ “ዛሬ ፍልስጥኤማውያን እኛን ድል ያደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር ስለምን ፈቀደላቸው? ከእኛ ጋር በመሄድ ከጠላቶቻችን እጅ ያድነን ዘንድ እንግዲህ እንሂድና የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከሴሎ እናምጣ።”