ዘኍል 10:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሖባብም “አይሆንም፤ እኔ ወደ ትውልድ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም መልሶ፣ “ይህስ አይሆንም፤ አልሄድም፤ ወደ አገሬና ወደ ወገኖቼ ተመልሼ እሄዳለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ ሀገሬና ወደ ዘመዶች እመለሳለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ አለው። |
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ታዲያ ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፤ ከእነርሱ ወደ አንደኛው ቀርቦ፥ ‘ልጄ ሆይ፥ ዛሬ ወደ ወይን አትክልት ቦታዬ ሄደህ እንድትሠራ ይሁን’ አለው።
“ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።
ከእንግዲህ ወዲህ እኛ ማንንም ሰው በሥጋዊ አመለካከት አንመለከትም፤ ከዚህ በፊት ክርስቶስንም የተመለከትነው እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋዊ አመለካከት ከሆነ ለወደፊቱ ግን ይህን አናደርግም።
እነዚህ ሁሉ በእምነት እንዳሉ ሞቱ፤ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውንም ነገር አላገኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይተው ልክ እንዳገኙት አድርገው በደስታ ተቀበሉት። በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውንም ተገነዘቡ።
አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው።
የሙሴ ዐማት የነበረው የቄናዊው ዘሮች ከይሁዳ ሕዝብ ጋር በመሆን የተምር ዛፎች ከሞሉባት ከኢያሪኮ ከተማ ተነሥተው፥ በይሁዳ ካለችው ከዐራድ በስተደቡብ ወዳለው ደረቅ ምድር ተጓዙ፤ እዚያም በዐማሌቃውያን መካከል ተቀመጡ።