Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 10:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ሙሴ የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ፥ ሆባብን “እነሆ፥ እግዚአብሔር ሊሰጠን ቃል ወደገባልን ምድር ለመሄድ ተዘጋጅተናል፤ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያበለጽግ ቃል ገብቶልናል፤ ስለዚህ አንተም ከእኛ ጋር አብረህ ሂድ፤ መልካም እናደርግልሃለን” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 በዚህ ጊዜ ሙሴ የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፣ “እነሆ፤ እግዚአብሔር፣ ‘እሰጣችኋለሁ’ ወዳለን ምድር ጕዞ ጀምረናል፤ በመልካም ሁኔታ ስለምናኖርህ ከእኛ ጋራ ሂድ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል በጎ ነገር ለማድረግ ቃል ገብቷልና አለው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን እንዲህ አለው፦ “ጌታ፦ ‘ለእናንተ እሰጣችኋለሁ’ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን፤ ጌታ ለእስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ሙሴም የሚ​ስ​ቱን አባት የም​ድ​ያ​ማ​ዊ​ውን የራ​ጉ​ኤ​ልን ልጅ ኦባ​ብን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ለእ​ና​ንተ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ ወዳ​ለው ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እስ​ራ​ኤል መል​ካ​ምን ነገር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መል​ካ​ምን እና​ደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለን” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፦ እግዚአብሔር፦ ለእናንተ እሰጠዋለሁ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን፤ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 10:29
31 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ።


ቀኔናዊው ሔቤር የሙሴ ዐማት ከነበረው ከሆባብ ልጆች ከቄናውያን ተለየ፤ ወደ ቃዴስ ቀረብ ብሎ በጸእናይም በሚገኘው በታላቁ ዛፍ አጠገብ ድንኳኑን ተከለ።


እነሆ፥ ሙሴ የምድያም ካህን የሆነውን የዐማቹን የየትሮንን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ መንጋውንም እየነዳ ከበረሓው ማዶ ወዳለው የእግዚአብሔር ተራራ እየተባለ ወደሚጠራው ወደ ሲና መጣ።


እነዚያም ሴቶች ልጆች ወደ አባታቸው ወደ ራጉኤል በተመለሱ ጊዜ “ዛሬ እንዴት በፍጥነት ተመለሳችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።


‘መልካም ነገር አደርጋለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛልሃለሁ’ ያልከውን አስታውስ።”


መንፈስ ቅዱስና ሙሽራይቱ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም “ና!” ይበል፤ የተጠማም ይምጣ፤ የፈለገም የሕይወትን ውሃ ያለ ምንም ዋጋ በነጻ ይጠጣ።


በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን።


ይህም እምነት በዘለዓለም ሕይወት ተስፋ ላይ የተመሠረተ ነው፤ የማይዋሸው አምላክ ይህን ሕይወት ለመስጠት ከዘመናት በፊት ቃል ገባልን።


ይሁን እንጂ የእግር ማሳረፊያ እንኳ የሚያኽል ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን ይህችን አገር ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ርስት አድርጎ እንደሚሰጠው ቃል ገብቶለት ነበር፤ ይህን ቃል የገባለትም አብርሃም ገና ልጅ ሳይኖረው ነበር።


ወደ ጽዮን የሚያደርሰውን መንገድ ይጠይቃሉ፤ አቅጣጫውንም ተከትለው ይጓዛሉ፤ ከእኔም ጋር ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ ከቶም አያፈርሱትም።


ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፦ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”


የእግዚአብሔርን ደግነት እዩና ቅመሱ፤ እርሱን ከለላ ያደረገ የተባረከ ነው።


“እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ቸርነት ስላደረጋችሁላቸው እናንተን ከአማሌቃውያን ጋር እንዳላጠፋ ከዐማሌቃውያን ተለይታችሁ ሂዱ” ብሎ ሳኦል ለቄናውያን ነገራቸው። እነርሱም ከዐማሌቃውያን ተለይተው ሄዱ።


የሙሴ ዐማት የነበረው የቄናዊው ዘሮች ከይሁዳ ሕዝብ ጋር በመሆን የተምር ዛፎች ከሞሉባት ከኢያሪኮ ከተማ ተነሥተው፥ በይሁዳ ካለችው ከዐራድ በስተደቡብ ወዳለው ደረቅ ምድር ተጓዙ፤ እዚያም በዐማሌቃውያን መካከል ተቀመጡ።


እግዚአብሔር እንደ ሰው አይዋሽም፤ ሐሳቡንም እንደ ሰው አይለውጥም የሰጠውን ተስፋ ሁሉ ይፈጽማል፤ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።


ሙሴም ዐማቱን በሰላም አሰናብቶት፤ ወደ አገሩ ተመለሰ።


የምድያም ካህን የሆነው የሙሴ ዐማት የትሮ፥ እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር መርቶ ባወጣቸው ጊዜ ለሙሴና ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገላቸውን ነገር ሁሉ ሰማ፤


እነርሱንም ከግብጻውያን እጅ ለማዳን ወርጃለሁ፤ ከግብጽም አውጥቼ አሁን ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገችውን ሰፊና ለም የሆነችውን ምድር እሰጣቸዋለሁ።


በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤


ይህን የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ ለዘለዓለምም የእናንተ ይሆናል፤


እንደ ስደተኞች ሆነው የሚኖሩባትን የከነዓንን ምድር ላወርሳቸው ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ።


ከዚህም በኋላ የትሮ የሙሴ ዐማት በሙሉ የሚቃጠል ቊርባንና ሌላም ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አመጣ፤ አሮንና የእስራኤል አለቆችም ሁሉ የተቀደሰውን ምግብ በአምልኮት ሥርዓት በእግዚአብሔር ፊት ለመመገብ ከሙሴ ዐማት ጋር መጡ።


እንግዲህ እስራኤላውያን ሰፈር ለቀው በየቡድናቸው የሚጓዙት በዚህ ቅደም ተከተል ነበር።


እግዚአብሔር አምላካችሁ ለዘለዓለም እንድትኖሩባት በሚያወርሳችሁ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖሩ ዘንድ ለእናንተና ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላቸው እኔ ዛሬ የማዛችሁን ሕጉንና ትእዛዞቹን ጠብቁ።”


በዚህም ዐይነት የቀድሞ አባቶችህ የነበሩበትን ምድር እንደገና ትወርሳለህ፤ እርሱም ከቀድሞ አባቶችህ ይበልጥ ባለጸጋና ቊጥርህ የበዛ እንድትሆን ያደርጋል።


ኑ፤ እግዚአብሔርን በመዝሙር እናመስግን! ለመዳናችን አምባም የድል እልልታ እናስተጋባለት!


በምድር ላይ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር “እልል!” በሉ!


አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን ይህችን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ መላውን የከነዓን ምድር ለዘለዓለም እንዲወርሱት ለዘርህ እሰጣለሁ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”


ሙሴም ከዚያ ሰው ጋር ለመኖር ፈቃደኛ ሆነ፤ ያም ሰው ልጁን ጺጳራን ሚስት ትሆነው ዘንድ ለሙሴ ሰጠው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios