ንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራው ጭምር፥ እንዲሁም የውሃ ማጠራቀሚያ ግድብ እንዴት እንደ ሠራና ወደ ከተማይቱ ውሃ ለማምጣት ያስቈፈረው የመሬት ውስጥ ቦይ አሠራር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።
ነህምያ 3:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የነበረው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር (ከዳዊት መቃብር ትይዩ ጀምሮ)፥ እስከ ኩሬ፤ እስከ ጀግኖች ሰፈር ድረስ ያለውን ክፍል ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም በኋላ የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዥ የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር ትይዩ እስከ ሰው ሠራሹ ኵሬና የጀግኖች ቤት ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን መልሶ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም በኋላ የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ በዳዊት መቃብር ፊት ለፊት እስካለው ስፍራ፥ እስከ ተሠራው መዋኛ ስፍራና እስከ ኃያላኑ ቤት ድረስ አደሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ የቤሶር ግዛት እኩሌታ ገዢ የዓዛቡህ ልጅ ነህምያ በዳዊት መቃብር አንጻር እስካለው ስፍራ፥ እስከ ተሠራውም መዋኛ፥ እስከ ኀያላኑም ቤት ድረስ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ የቤትጹር ግዛት እኩሌታ አለቃ የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ በዳዊት መቃብር አንጻር እስካለው ስፍራ፥ እስከ ተሠራውም መዋኛ፥ እስከ ኃያላኑም ቤት ድረስ አደሰ። |
ንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራው ጭምር፥ እንዲሁም የውሃ ማጠራቀሚያ ግድብ እንዴት እንደ ሠራና ወደ ከተማይቱ ውሃ ለማምጣት ያስቈፈረው የመሬት ውስጥ ቦይ አሠራር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።
ሬሳውም በልዩ ቅመማ ቅመምና በሽቶ ታሽቶ እርሱ ራሱ በዳዊት ከተማ ከአለት አስፈልፍሎ ባሠራው መቃብር ተቀበረ፤ ስለ ክብሩም ብዙ እንጨት ከምረው በማንደድ ታላቅ ለቅሶ አደረጉለት።
ቀጥሎም ከከተማይቱ በስተ ምሥራቅ በኩል በሰሜን ወደሚገኘው “የውሃ ምንጭ ቅጽር በር” ተብሎ በሚጠራው ስፍራና ወደ ንጉሡ ኲሬ ሄድኩ፤ ነገር ግን ተቀምጬበት የነበረው እንስሳ የፍርስራሹን ክምር ለማለፍ የሚያስችለው መንገድ ማግኘት አልቻለም።
የቤትሀካሬም ወረዳ ገዢ የሆነው የሬካብ ልጅ ማልኪያ የጒድፍ መጣያውን ቅጽር በር በማደስ ሠራ፤ በሮችን ገጠመ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጀ።
በቅጽሩ ሥራ ተካፋዮች የነበሩት ሌዋውያን ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦ የባኒ ልጅ ረሑም ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው ሐሻብያ ወረዳውን በመወከል ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ።
ከጥንቱ ኲሬ የሚወርደውን ውሃ ለመመለስ በከተማይቱ ውስጥ ግድብ ሠራችሁ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በመጀመሪያ ዐቅዶ ያደረገው እግዚአብሔር መሆኑ ትዝ አላላችሁም።
እግዚአብሔርም ኢሳይያስን እንዲህ አለው፦ “አንተና ልጅህ ሼርያሹብ ንጉሥ አካዝን ለመገናኘት ውጡ፤ እርሱንም ከላይኛው ኩሬ ውሃ በሚመጣበት በልብስ አጣቢዎች ቦታ ታገኙታላችሁ።
“ወንድሞቼ ሆይ! ከቀድሞ አባቶች አንዱ የሆነው ዳዊት እንደ ሞተና እንደ ተቀበረ፥ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ እንዳለ በግልጥ ልንገራችሁ።