ነህምያ 12:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም በዓል ለማክበር የሌዋውያኑ ቤተሰቦች መዘምራን ሁሉ ሰፍረው ከነበሩበት ከኢየሩሳሌም አካባቢና በነጦፋ ከሚገኙት ታናናሽ ከተሞች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መዘምራኑንም እንደዚሁ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለው ከነጦፋውያን መንደሮች በአንድነት ሰበሰቧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመዘምራኑ ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙሪያና ከነጦፋውያን መንደሮች፥ ተሰበሰቡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመዘምራኑም ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙርያና ከሌሎችም መንደሮች ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መዘምራኑም በኢየሩሳሌም ዙሪያ መንደሮች ሠርተው ነበርና የመዘምራኑ ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙሪያና ከነጦፋውያን መንደሮች፥ ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ከዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ። |
እንዲሁም አገልግሎቱን የሚፈጽሙት የቤተ መቅደሱ መዘምራንና ሌሎችም ሌዋውያን ኢየሩሳሌምን ለቀው በመውጣት ወደየእርሻቸው ተመልሰው መግባታቸውን ተገነዘብኩ፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሕዝቡ ለመዘምራኑና ለሌዋውያኑ በቂ መተዳደሪያ ባለመስጠታቸው ነበር።
ከዚህም የተነሣ ሰንባላጥና ጌሼም በተለይ ኦኖ ተብሎ በሚጠራው ሜዳ ከሚገኙት መንደሮች በአንዲቱ እንድንገናኛቸው መልእክት ላኩብኝ፤ ይህም እኔን ለመጒዳት በተንኰል የተዶለተ ዘዴ ነበር።
የቀድሞ አባቶቻቸው ከዚህ በሚከተሉት ከተሞች የሚኖሩም ከምርኮ ተመልሰዋል፦ በቤተልሔምና በነጦፋ የሚኖሩ 188 በዐናቶት የሚኖሩ 128 በቤት ዓዝማዌት የሚኖሩ 42 በቂርያትይዓሪም፥ በከፊራና በበኤሮት የሚኖሩ 743 በራማና በጌባዕ የሚኖሩ 621 በሚክማስ የሚኖሩ 122 በቤትኤልና በዐይ የሚኖሩ 123 በሁለተኛይቱ ነቦ የሚኖሩ 52 በሁለተኛይቱ ዔላም የሚኖሩ 1254 በሓሪም የሚኖሩ 320 በኢያሪኮ የሚኖሩ 345 በሎድ፥ በሐዲድና በኦኖ የሚኖሩ 721 በሰናአ የሚኖሩ 3930