ሚክያስ 6:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕዝቤ ሆይ! ምን አደረግሁህ? ያከበድኩብህስ ነገር ምንድን ነው? እስቲ መልስልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቤ ሆይ፤ ምን አድርጌሃለሁ? ሸክም የሆንሁብህስ እንዴት ነው? እስኪ መልስልኝ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቤ ሆይ፥ ምን አደረግሁህ? ያደከምኩህስ እንዴት ነው? መልስልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤ ሆይ፥ ምን አድርጌለሁ? በምንስ አድክሜሃለሁ? መስክርብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቤ ሆይ፥ ምን አድርጌለሁ? በምንስ አድክሜሃለሁ? መስክርብኝ። |
እኔ ያመፅኩት በአንተ ላይ ነው፤ የበደልኩትም አንተን ብቻ ነው፤ አንተ የምትጠላውን ነገር አደረግሁ፤ ስለዚህ በእኔ ላይ መፍረድህና እኔንም መቅጣትህ ትክክል ነው።
ለመሆኑ እኔ ለእርሱ ያላደረግኹለት ነገር አለን? ከዚህስ ሌላ ላደርግለት የሚገባ ምን አለ? ታዲያ፥ መልካም ፍሬ ያፈራል ብዬ ስጠብቀው ስለምን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ?
እናንተ በዚህ ዘመን ያላችሁ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እኔ እግዚአብሔር የምላችሁን አድምጡ፤ እኔ ለእናንተ እንደ በረሓ፥ ወይም በድቅድቅ ጨለማ እንደ ተሞላ ምድር ሆንኩባችሁን? ታዲያ ‘እኛ የፈለግነውን እናደርጋለን እንጂ ከቶ ወደ አንተ አንመለስም’ የምትሉን ለምንድን ነው?
እነሆ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኔ ርቀው የሄዱት በኔ ላይ ምን ጥፋት አግኝተው ነው? እነርሱም ከንቱ የሆኑትን ጣዖቶች በማምለካቸው ራሳቸውን ከንቱዎች አደረጉ።
ሕዝቤ ሆይ! የሞአብ ንጉሥ ባላቅ ምን እንደ ዐቀደብህና የቢዖር ልጅ በለዓም ምን እንደ መለሰለት አስታውስ፤ ከሺጢም ተነሥተህ ወደ ጌልጌላ በምትሄድበት ጊዜ በመንገድ ላይ የሆነውን ሁሉ አስታውስ፤ ይህን ሁሉ ብታስታውስ አንተን ለማዳን ያደረግኹትን ሁሉ ታውቃለህ።”
የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።