ማቴዎስ 7:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጠይቁ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለምኑ፤ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፤ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፤ ይከፈትላችሁማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። |
እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅሱም፤ እግዚአብሔር ርኅሩኅ ስለ ሆነ የእርሱን ርዳታ በመፈለግ በምትጮኹበት ጊዜ ሰምቶ መልስ ይሰጣችኋል።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ ከአሁን በፊት የማታውቃቸውን ተመርምሮ ሊደረሰባቸው የማይችሉትን ታላላቅ ነገሮች እገልጥልሃለሁ።
እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፥ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠትን ካወቃችሁ፤ ታዲያ፥ በሰማይ ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን አይሰጣቸውም!
የቤቱ ጌታ ተነሥቶ በሩን ይዘጋዋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ በሩን በማንኳኳት፥ ‘ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ ማለት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም!’ ሲል ይመልስላችኋል።
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።
ኢየሱስም “የእግዚአብሔርን ስጦታና ‘ውሃ አጠጪኝ!’ የሚልሽ ማን እንደ ሆነ ብታውቂው ኖሮ፥ እርሱን መለመን የሚገባሽ አንቺ ነበርሽ፤ እርሱም የሕይወትን ውሃ ይሰጥሽ ነበር” አላት።
ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሰው እግዚአብሔር መኖሩንና እርሱን ለሚፈልጉት ሰዎችም ስጦታን የሚሰጥ መሆኑን ማመን አለበት።
እንዲህ ዐይነቱ በእምነት ላይ የተመሠረተ ጸሎት በሽተኛውን ያድነዋል፤ ጌታም ከበሽታው ይፈውሰዋል፤ የሠራው ኃጢአትም ቢኖር ይቅር ይባልለታል።