ማቴዎስ 7:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፥ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠትን ካወቃችሁ፤ ታዲያ፥ በሰማይ ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን አይሰጣቸውም! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁበት፣ የሰማዩ አባታችሁ ታዲያ ለሚለምኑት መልካም ስጦታን እንዴት አብልጦ አይሰጥ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካም ነገርን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? |
የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ይህም በዐይንህ ፊት ያነሰ ሆኖ አሁንም የበለጠ ነገር እያደረግህ ነው፤ ስለ ባሪያህ ልጆች ለሚመጡት ዘመናት ብዙ የተስፋ ቃል ተናግረሃል፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ይህ ለሰው ሁሉ የተለመደ ድርጊትህ ነውን?
ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፦ “እናት የምታጠባውን ልጅዋን ልትረሳ ትችላለችን? ወይስ ለወለደችው ልጅ አትራራምን? እርስዋ እንኳ ብትረሳ እኔ ግን እናንተን አልረሳም።
ለእኛ ስላደረጋቸው ድርጊቶች ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ እንደ መሐሪነቱ ስላሳየው ከፍተኛ በጎ አመለካከት፥ ስለ ተትረፈረፈውም ዘለዓለማዊ ፍቅሩ የእግዚአብሔርን ቸርነት ምስጉን ድርጊቶቹን እዘረዝራለሁ።
የኑዛዜ ቃል ይዛችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እንዲህም በሉት፦ “ኃጢአታችንን ሁሉ ይቅር በለን፤ በምሕረት ተቀበለን፤ እኛም የአንደበታችን መልካም ፍሬ የሆነውን ምስጋና እናቀርብልሃለን።
ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በቀሪውም ሕዝቡ ላይ በደልን የማይቈጥር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረት ማድረግ ስለሚያስደስትህ ቊጣህ ለዘለዓለም የሚቈይ አይደለም።
የሠራዊት አምላክ ካህናቱን እንዲህ ይላቸዋል፦ “ልጅ አባቱን፥ አገልጋይም አሳዳሪ ጌታውን ያከብራል፤ እነሆ፥ እኔ አባታችሁ ከሆንኩ ለምን አታከብሩኝም? ጌታችሁም ከሆንኩ ለምን ክብር አትሰጡኝም? እናንተ የእኔን ስም ንቃችኋል፤ ነገር ግን ‘ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ።
የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።
ታዲያ፥ እኛ አይሁድ ከአሕዛብ እንበልጣለን ማለት ነውን? ከቶ አይደለም! ሰዎች ሁሉ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ኃጢአተኞች መሆናቸውን ቀደም ብዬ አስረድቻለሁ።
ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ እንዲሰጥ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው ዓለም በሙሉ ለኃጢአት በመገዛት የኃጢአት እስረኛ ሆኖአል።
መልካም ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሚመጣው እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከብርሃን አባት ከእግዚአብሔር ነው።
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ! በእርግጥም የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ዓለም እግዚአብሔርን ስላላወቀ እኛንም አያውቀንም።
ፍቅር ማለት እንዲህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን ስለ ወደድነው ሳይሆን እርሱ ስለ ወደደንና ኃጢአታችንን እንዲደመስስ ልጁን ስለ ላከልን ነው።