ማቴዎስ 28:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ አንዳዶቹ ግን ተጠራጠሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ ጥቂቶች ግን ተጠራጠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባዩትም ጊዜ ሰገዱ፤ አንዳዶቹ ግን ተጠራጠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ። |
ከዚያም በኋላ ዐሥራ አንዱ በማእድ ቀርበው ሲበሉ ኢየሱስ ተገለጠላቸው፤ “ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ በሕይወት አለ፤ በዐይናችንም አይተነዋል፤” ብለው የነገሩአቸውን ባለማመናቸውና በግትርነታቸው ነቀፋቸው።
ይህንንም ያደረገው ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ፥ እንዲሁም ወልድን እንዲያከብሩ ነው፤ ወልድን የማያከብር፥ ወልድን የላከውን አብን አያከብርም።
ብዙ መከራ ተቀብሎ ከሞተ በኋላ በብዙ ግልጥ ማስረጃዎች ሕያው ሆኖ ታያቸው፤ አርባ ቀን ሙሉ እየተገለጠላቸውም ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አስተማራቸው።