ማቴዎስ 28:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ እንዲሄዱ ወደ አመለከታቸው፥ በገሊላ ወደሚገኘው ተራራ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዐሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት በገሊላ ወዳለው ኢየሱስ ወዳመለከታቸው ተራራ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ ወዳዘዛቸው ተራራ ወደ ገሊላ ሄዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ኢየሱስ ወዳዘዛቸው ተራራ ወደ ገሊላ ሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ኢየሱስ ወዳዘዛቸው ተራራ ወደ ገሊላ ሄዱ፥ |
እንግዲህ በፍጥነት ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ‘ከሞት ተነሥቶአል! እነሆ፥ ወደ ገሊላ ቀድሞአችሁ ይሄዳል፤ በዚያ ታገኙታላችሁ!’ ብላችሁ ንገሩአቸው፤ እነሆ፥ ነግሬአችኋለሁ።”
እነርሱ ኢየሱስ በገሊላ በነበረበት ጊዜ፥ ይከተሉትና ያገለግሉት ነበር። እንዲሁም ከኢየሱስ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ብዙ ሌሎች ሴቶች ነበሩ።
ከዚያም በኋላ ዐሥራ አንዱ በማእድ ቀርበው ሲበሉ ኢየሱስ ተገለጠላቸው፤ “ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ በሕይወት አለ፤ በዐይናችንም አይተነዋል፤” ብለው የነገሩአቸውን ባለማመናቸውና በግትርነታቸው ነቀፋቸው።
አሁንም ሂዱ፤ ለደቀ መዛሙርቱና ለጴጥሮስ ‘ከዚህ በፊት ኢየሱስ እንደ ነገራችሁ እርሱ ወደ ገሊላ ቀድሞአችሁ ይሄዳል፤ በዚያም ታዩታላችሁ፤’ ብላችሁ ንገሩአቸው።”
ደግሞም እግዚአብሔር ክርስቶስን ከሞት አስነሥቶታል ብለን በማስተማራችን ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነናል ማለት ነው፤ እንግዲህ የሞቱት ሰዎች ከሞት ካልተነሡ እግዚአብሔር ክርስቶስንም ከሞት አላስነሣውም ማለት ነው።