‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
ማቴዎስ 21:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የጽዮን ከተማ ለምትባለው ለኢየሩሳሌም፦ ‘እነሆ! ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ በአህያይቱና በውርንጫዋ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል!’ ብላችሁ ንገሩአት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለጽዮን ልጅ እንዲህ በሏት፤ ‘እነሆ፤ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፣ በአህያዪቱና በግልገሏ፣ በውርንጫዪቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለጽዮን ልጅ “እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፥ በሉአት።” |
‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
ንጉሥ ዳዊትም “ይህ ሁሉ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “ንጉሥ ሆይ! አህዮቹን ያመጣኋቸው ቤተሰብህ እንዲቀመጡባቸው፥ ዳቦውና ፍራፍሬውም ለተከታዮችህ ስንቅ እንዲሆኑና የወይን ጠጁም በምድረ በዳ በሚደክሙበት ጊዜ እንዲጠጡት ነው” ሲል መለሰ።
ንጉሡም እንዲህ አላቸው፦ “በቤተ መንግሥቴ ከሚገኙት ባለሟሎቼ ጋር አብራችሁ ሂዱ፤ ልጄን ሰሎሞንንም እኔ በምቀመጥባት በቅሎ አስቀምጡትና አጅባችሁት ወደ ግዮን ምንጭ ውረዱ፤
ሰሎሞንም ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ ከእነርሱም ከፊሉ ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም፥ ሌሎቹ ደግሞ በልዩ ልዩ ከተሞች ተመድበው እንዲኖሩ አደረገ፤
ለጽዮን መልካም ነገርን የምታበሥሩ ሆይ! ወደ ከፍተኛ ተራራ ውጡ! እናንተ ለኢየሩሳሌም መልካም ዜናን የምታበሥሩ ሆይ! ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ! ጮክ በሉ አትፍሩ! ለይሁዳ ከተሞች፥ “እነሆ፥ አምላካችሁ” በሉ።
እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ እንዲህ ብሎ ያውጃል፦ “አዳኝሽ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር ለሰዎች የሚከፍለው ዋጋና ሽልማት አለ ብላችሁ ለጽዮን ልጅ ንገሩአት።”
ለይሁዳ ሕዝቦች ግን ፍቅር አሳያቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ፤ የማድናቸውም በጦርነት ኀይል አይደለም፤ በሰይፍ፥ በቀስትና በፍላጻ ወይም በፈረስና በፈረሰኛ አይደለም።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በኤፍራታ ምድር የምትገኚ ቤተልሔም ሆይ! ከይሁዳ ትናንሽ ከተሞች አንድ ብትሆኚም እንኳ ከአንቺ አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ የእስራኤልን ሕዝብ የሚመራ ገዢ ይወጣልኛል።”
‘በይሁዳ ክፍለ ሀገር የምትገኚ አንቺ ቤተልሔም ሆይ! ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መሪ ከአንቺ ስለሚወጣ፥ ከይሁዳ ታላላቅ ከተሞች በምንም አታንሺም።’ ”
እኔ ጳውሎስ በእናንተ ፊት ሳለሁ ትሑት ተባልኩ፤ ከእናንተ ስርቅ ግን በእናንተ ላይ ደፋር ተባልኩ፤ በክርስቶስ ቸርነትና ደግነት እለምናችኋለሁ፤
ያም ንጉሥ ለሠራዊቱ ብዙ ፈረሶች ያሉት መሆን የለበትም፤ እግዚአብሔር ሕዝቡ ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ስለ አዘዘ ፈረሶችን ለመግዛት ወደ እዚያ ሰዎችን አይላክ።
ዓብዶን በሰባ አህዮች ላይ ተቀምጠው የሚጋልቡ አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ የልጅ ልጆች ነበሩት፤ ዓብዶን ስምንት ዓመት የእስራኤል መሪ ሆነ።
እናንተ ኮርቻ በተጫኑ በነጫጭ አህዮች ላይ ተቀምጣችሁ የምትጓዙ፥ እናንተ በምቹና በአማረ ግላስ ላይ የምትንደላቀቁ፥ እናንተ በእግር የምትንሸራሸሩ፥ ስለዚህ ነገር ተናገሩ።