ማቴዎስ 20:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፤ እነርሱም ያላግጡበታል፤ ይገርፉታል፤ ይሰቅሉታልም፤ ግን በሦስተኛው ቀን ከሞት ይነሣል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲያላግጡበት፣ እንዲገርፉትና እንዲሰቅሉት ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሣል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲያላግጡበት፥ እንዲገርፉትና እንዲሰቅሉት ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው። |
ሙታንህ ተነሥተው ሕያዋን ይሆናሉ፤ እናንተ በመቃብር ውስጥ የምትኖሩ፥ ተነሥታችሁ የደስታ መዝሙር ዘምሩ! አንጸባራቂው ጠል ምድርን እንደሚያድስ እግዚአብሔርም ከሞቱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን ተነሥተው በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል።
እርሱም በሌሎች የተናቀና የተጠላ ነበር፤ እርሱ የመከራና የሐዘን ሰው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እስኪያዞሩበት ድረስ እርሱ የተናቀ፥ እኛም ያላከበርነው ሰው ነበር።
ዮናስ በዓሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንዳሳለፈ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ያሳልፋል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ይላቸው ጀመር፦ “ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ አለብኝ፤ እዚያም ከሽማግሌዎች፥ ከካህናት አለቆችና ከሕግ መምህራን መከራ ይደርስብኛል፤ ይገድሉኛል፤ ግን በሦስተኛው ቀን እነሣለሁ።”
አንዳንዶችም ምራቃቸውን እንትፍ ይሉበት ጀመር፤ ዐይኑንም በጨርቅ ሸፍነው “አንተ ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደ መታህ ዕወቅ!” እያሉ በቡጢ ይመቱት ነበር። ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።
ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፥ ከሕግ መምህራን፥ ከሸንጎውም አባሎች ሁሉ ጋር ተማከሩ፤ ከዚያም በኋላ ኢየሱስን አስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።
እርሱም ራሱ እግዚአብሔር አስቀድሞ ባቀደውና ባወቀው አሠራር መሠረት ለእናንተ ተላልፎ ተሰጠ፤ እናንተም በዐመፀኞች እጅ እንዲሰቀልና እንዲሞት አደረጋችሁት።
ይህ ነቢይ ወደ እኛ ቀረበ፤ የጳውሎስን መታጠቂያ ወስዶ የገዛ እጆቹንና እግሮቹን አሰረና “መንፈስ ቅዱስ የዚህን መታጠቂያ ባለቤት በኢየሩሳሌም ያሉ አይሁድ እንደዚህ አስረው ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል ይላል” አለ።
“በእርግጥም ሄሮድስና ጴንጤናዊ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው መሲሕ ባደረግኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሡ፤