አምላክ ሆይ! ለምን መንገድህን እንድንስት አደረግኸን? እንዳንፈራህስ ለምን ልባችንን አደነደንክ? ለአገልጋዮችህ፥ የአንተ ስለ ሆኑት ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።
ማርቆስ 8:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም ይህንኑ ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እንጀራ ስለሌለን ነው ብላችሁ ስለምን ታስባላችሁ? ገና ምንም የማታስተውሉና የማይገባችሁ ናችሁን? ልባችሁስ ገና እንደ ደነዘዘ ነውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ “እንጀራ ስለሌለን ነው በማለት የምትነጋገሩት ስለ ምንድን ነው? አሁንም አታስተውሉምን? ልብ አትሉምን? ወይስ ልባችሁ ደንድኗል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ፥ እንዲህ አላቸው፤ “እንጀራ ስለሌለን ነው በማለት ምን ያነጋግራችኋል? አሁንም አታስተውሉምን? ልብ አትሉምን? ወይስ ልባችሁ ደንድኗል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም አውቆ እንዲህ አላቸው “እንጀራ ስለሌላችሁ ስለ ምን ትነጋገራላችሁ? ገና አልተመለከታችሁምን? አላስተዋላችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም አውቆ እንዲህ አላቸው፦ እንጀራ ስለሌላችሁ ስለ ምን ትነጋገራላችሁ? ገና አልተመለከታችሁምን? አላስተዋላችሁምን? |
አምላክ ሆይ! ለምን መንገድህን እንድንስት አደረግኸን? እንዳንፈራህስ ለምን ልባችንን አደነደንክ? ለአገልጋዮችህ፥ የአንተ ስለ ሆኑት ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።
ከዚያም በኋላ ዐሥራ አንዱ በማእድ ቀርበው ሲበሉ ኢየሱስ ተገለጠላቸው፤ “ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ በሕይወት አለ፤ በዐይናችንም አይተነዋል፤” ብለው የነገሩአቸውን ባለማመናቸውና በግትርነታቸው ነቀፋቸው።
ኢየሱስም ስለ ልባቸው ድንዛዜ አዝኖ በዙሪያው ያሉትን በቊጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነለት።
አንተ ሁሉን እንደምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊያቀርብልህ እንደማያስፈልግህ አሁን ዐወቅን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ወጣህ እናምናለን።”
ሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፥ እኔ እንደምወድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “በጎቼን አሰማራ፤
ልጆችዋንም በሞት እቀጣለሁ፤ አብያተ ክርስቲያንም ሁሉ የሰውን ሐሳብና ምኞት የምመረምር እኔ መሆኔን ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደየሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።