ማርቆስ 15:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ አሁንም ኢየሱስ ምንም መልስ አልሰጠም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰም፤ ጲላጦስ ተገረመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰም፤ ጲላጦስ ተገረመ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ከዚያ በኋላ ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም አልመለሰም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ከዚያ በኋላ ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም አልመለሰም። |
“እርሱ ግፍና ችግር ደረሰበት፤ ይሁን እንጂ ምንም አልተናገረም፤ ለመታረድ እንደሚወሰድ ጠቦትና በሸላቾቹ ፊት ጸጥ እንደሚል በግ ዝም አለ እንጂ ምንም አልተናገረም።
ሊቀ ካህናት ኢያሱ ሆይ! ይህን ስማ፤ እናንተም ከእርሱ ጋር በክህነት የምታገለግሉና ወደ ፊት ለሚሆነው መልካም ነገር ምልክት የምትሆኑ ይህን አድምጡ፤ ‘ቅርንጫፍ’ ተብሎ የሚጠራውን አገልጋዬን ወደ ፊት እልካለሁ።
እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት ተፈርዶባቸው ወደሚገደሉበት ቦታ ከሚወሰዱት ሰዎች መካከል የመጨረሻዎቹ ያደረገን ይመስለኛል፤ ከዚህም የተነሣ በዓለም ሁሉ በመላእክትም ሆነ በሰዎች ፊት እንደ ትርኢት ሆነን እንታያለን፤