ጴጥሮስ ከቤት ውጪ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ በዚያን ጊዜ አንዲት ገረድ ወደ እርሱ ቀርባ “አንተም ከገሊላዊው ኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው።
ሉቃስ 23:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጲላጦስም ገሊላ የሚለውን ቃል በሰማ ጊዜ፥ “ይህ የገሊላ ሰው ነውን?” ብሎ ጠየቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጲላጦስም ይህን ሲሰማ፣ ሰውየው የገሊላ ሰው መሆኑን ለማረጋገጥ ጠየቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጲላጦስም ይህንን ሰምቶ ሰውየው የገሊላ ሰው እንደሆነ ጠየቀ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጲላጦስም “ገሊላ” ሲሉ ሰምቶ፤ ሰውየዉ ገሊላዊ እንደ ሆነ የገሊላን ሰዎች ጠየቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጲላጦስ ግን፦ ገሊላ ሲሉ በሰማ ጊዜ፦ የገሊላ ሰው ነውን? ብሎ ጠየቀ፤ |
ጴጥሮስ ከቤት ውጪ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ በዚያን ጊዜ አንዲት ገረድ ወደ እርሱ ቀርባ “አንተም ከገሊላዊው ኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው።
በዚያን ጊዜ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጥተው፥ “የገሊላ ሰዎች መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ጊዜ ጲላጦስ ገደላቸው፤ ደማቸውም ከመሥዋዕታቸው ጋር አደባለቀ” ሲሉ ነገሩት።
ከዚያም በኋላ የሕዝብ ቈጠራ በተደረገበት ዘመን ገሊላዊው ይሁዳ ተነሥቶ ብዙ ሰዎች እንዲከተሉት አድርጎ ነበር፤ እርሱም ተገደለ፤ የተከተሉትም ሁሉ ተበታተኑ።