ሉቃስ 23:54 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረገው ዓርብ ማታ ለሰንበት ዝግጅት በሚደረግበት ጊዜ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕለቱ ሰንበት ሊገባ ስለ ነበር፣ የመዘጋጃ ቀን ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመዘጋጀት ቀንም ነበረ፤ ሰንበትም እየጀመረ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ቀን የሰንበት መግቢያ ዐርብ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመዘጋጀት ቀንም ነበረ፤ ሰንበትም ሊጀምር ነበረ። |
ከዚህ በኋላ የአይሁድ ባለሥልጣኖች፥ የተሰቀሉትን ሰዎች ጭን ሰብረው፥ አስከሬናቸውን ከመስቀል እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት የሰንበት ዝግጅት ቀን ስለ ነበረና ያ ሰንበትም ትልቅ በዓል ስለ ሆነ፥ በሰንበት ቀን ሥጋቸው በመስቀል ላይ እንዳይሆን ነበር።