ሉቃስ 15:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፥ እነሆ፥ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶ ነበር፤ ተገኘ’፤ መደሰትም ጀመሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶም ነበር፤ ተገኝቷል።’ ከዚያም ይደሰቱ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም።’ ደስ ይላቸውም ጀመር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኖአልና፥ ጠፍቶም ነበር፤ ተገኝቶአልና ደስ ይላቸውም ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይላቸው ጀመር። |
እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።
“የጠፉትን እፈልጋለሁ፤ የባዘኑትን እመልሳለሁ፤ የተሰበሩትን እጠግናለሁ፤ ደካሞችን አበረታለሁ፤ እኔ ትክክለኛ እረኛ ስለ ሆንኩ በግፍ የሰቡትንና ብርቱዎች የሆኑትን አጠፋለሁ።
የደከሙትን አላበረታቸሁም፤ የታመሙትን አላዳናችሁም፤ የተሰበሩትን አልጠገናችሁም፤ የባዘኑትን አልመለሳችሁም፤ የጠፉትን አልፈለጋችሁም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በግፍና በጭካኔ ገዛችኋቸው።
“ከእናንተ መካከል መቶ በግ ያለው ሰው ከመቶዎቹ አንድ በግ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ የጠፋውን እስኪያገኝ ድረስ ለመፈለግ የማይሄድ ማነው?
እግዚአብሔር እነርሱን በጣላቸው ጊዜ ሌላው የዓለም ሕዝብ ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቀ እግዚአብሔር እነርሱን በሚቀበላቸው ጊዜ ምን የሚሆን ይመስላችኋል? ይህማ ከሞት እንደ መነሣት ያኽል ነው!
እንዲሁም የሰውነታችሁን ክፍሎች የዐመፅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታስገዙ፤ ነገር ግን ከሞት ተነሥታችሁ ሕያዋን እንደ ሆናችሁ በማድረግ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ የሰውነታችሁንም ክፍሎች ሁሉ የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አስገዙ።
አንዱ የአካል ክፍል ሲሠቃይ ሌሎችም የአካል ክፍሎች በሙሉ አብረው ይሠቃያሉ፤ አንዱ የሰውነት ክፍል ሲከበር ሌሎቹም የሰውነት ክፍሎች አብረው ከእርሱ ጋር ይደሰታሉ።
ኃጢአት በመሥራታችሁና የኃጢአተኛው ሥጋችሁ በክርስቶስ በማመን ባለመገረዙ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሕያዋን አድርጓችኋል፤ ኃጢአታችሁንም ሁሉ ይቅር ብሎላችኋል።
እነዚህ ሰዎች ያለ ኀፍረት በመዳራት በአንድነት ግብዣችሁ ላይ ሲገኙ እንቅፋት ይሆኑባችኋል፤ እነርሱ የሚያስቡት ስለ ራሳቸው ብቻ ነው፤ በነፋስ እንደሚገፋ፥ ዝናብ እንደሌለው ደመና ናቸው። በፍሬ ወራት እንኳ ፍሬ እንደማይገኝበት፥ ከስሩ እንደ ተነቀለና ሁለት ጊዜ እንደ ሞተ ዛፍ ናቸው።
“ለሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ ሰባቱን የእግዚአብሔር መንፈሶችና ሰባቱን ኮከቦች ከያዘው የተነገረ ነው፤ ሥራህን ዐውቃለሁ፤ በስም ሕያው ነህ፤ ነገር ግን ሞተሃል።