Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 66:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ይህንንም የምታደርጉት ከመጽናኛ ጡትዋ ጠብታችሁ ትጠግቡ ዘንድ፥ ከተከበረው ደረትዋ የተትረፈረፈውን ወተት ጠጥታችሁ ትደሰቱ ዘንድ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከሚያጽናኑ ጡቶቿ፣ ትጠባላችሁ፤ ትረካላችሁም፤ እስክትረኩም ትጠጣላችሁ፤ በተትረፈረፈ ሀብቷም ትደሰታላችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንድትጠቡ ከማጽናናትዋም ጡት እንድትጠግቡ፥ እጅግ ጠጥታችሁ በክብርዋ ሙላት ደስ እንዲላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ትጠቡ ዘንድ ከማ​ጽ​ና​ና​ቷም ጡት ትጠ​ግቡ ዘንድ እጅግ ጠጥ​ታ​ችሁ በክ​ብ​ርዋ ሙላት ደስ ይላ​ችሁ ዘንድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ትጠቡ ዘንድ ከማጽናናትዋም ጡት ትጠግቡ ዘንድ፥ እጅግ ጠጥታችሁ በክብርዋ ሙላት ደስ ይላችሁ ዘንድ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 66:11
9 Referencias Cruzadas  

በቤትህ የተትረፈረፈውን ምግብ ይጋበዛሉ፤ አስደሳች ከሆነ ወንዝህም ታጠጣቸዋለህ።


ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል። የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቂአለሽ፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት የሚጠባበቁ ከቶ አያፍሩም።”


ኢየሩሳሌም ሆይ! ብርሃንሽ ስለ መጣ ተነሺና አብሪ፤ የእግዚአብሔርም ክብር በአንቺ ላይ ያበራል።


ልጆች የእናታቸውን ጡት እንደሚጠቡ የአንቺም ልጆች የሕዝቦችንና የነገሥታትን ሀብት በመውሰድ ይጠቀሙበታል፤ አንቺም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ ኀያሉ የያዕቆብ አምላክ መሆኔን ታውቂአለሽ።


እነሆ፥ ጨለማ ምድርን፥ ድቅድቅ ጨለማም ሕዝብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ላይ ያበራል፤ ክብሩም በአንቺ ላይ ይገለጣል።


ይህንንም አይተሽ ፈገግታሽ በደስታ ይፈካል፤ ከባሕር የሚገኘው በረከትና፥ ከሕዝቦች የሚመጣው ሀብት የአንቺ ስለሚሆን፥ ከደስታሽ ብዛት የተነሣ ልብሽ ይፈነድቃል።


ሕዝቦች የሚሰጥሽን ፍርድ፥ ነገሥታትም ክብርሽን ያያሉ፤ አንቺም እግዚአብሔር በሚያወጣልሽ አዲስ ስም ትጠሪአለሽ።


“በዚያን ጊዜ ተራራዎችም ሁሉ በወይን ተክል ይሸፈናሉ፤ በኰረብቶችም ላይ ብዙ ወተት የሚሰጡ ከብቶች ይሰማራሉ፤ በይሁዳ ምድር የሚገኙ ወንዞች ሁሉ በውሃ የተሞሉ ይሆናሉ፤ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ምንጭ ይፈልቃል፤ የሺጢምንም ሸለቆ ያጠጣል።


አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ወተት እንደሚመኙ እናንተም ለመዳን እያደጋችሁ የምትሄዱበትን ንጹሑን መንፈሳዊ ትምህርት ተመኙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos