ሉቃስ 1:70 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥንት ዘመን ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ጥንት በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥንት ጀምሮ በነበሩ በቅዱሳን በነቢያት አፍ እንደ ተናገረ። |
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”
‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከዳዊት ዘር መካከል ጻድቅ የሆነውን ለንጉሥነት የምመርጥበት ጊዜ ይመጣል፤ ያም ንጉሥ በጥበብ ያስተዳድራል፤ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ትክክልና ቅን የሆነውን ነገር ያደርጋል።
የአገልጋዬ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ፥ አትፍሩ ተስፋም አትቊረጡ፤ ከሩቅ አገር በደኅና እመልሳችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ተማርከው ከተወሰዱበት አገር እመልሳቸዋለሁ፤ እስራኤላውያን እንደገና ሰላም አግኝተው ያለ ስጋት ይኖራሉ።
ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ፥ ‘እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ)፥ ጠላቶችህን በእግርህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤’ ብሎታል።
ኢየሱስም፥ “ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ለሙሴ በተሰጠው ሕግ፥ በነቢያትና በመዝሙር መጻሕፍት ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም አለበት ብዬ የነገርኳችሁ ቃል ይህ ነው” አላቸው።
እነርሱም እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ተለያዩ። ሆኖም ከመለያየታቸው በፊት ጳውሎስ ለመጨረሻ ጊዜ ሲናገር እንዲህ አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ አማካይነት ለአባቶቻችሁ የተናገረው ልክ ነበር!
እነዚህ ነቢያት ያገለግሉ የነበሩት እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳልነበረ ተገልጦላቸዋል፤ ያገለገሉአችሁም ከሰማይ በተላከው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት አሁን ወንጌልን ያበሠሩአችሁ ሰዎች የነገሩአችሁን በመግለጥ ነው፤ ይህን ነገር መላእክት እንኳ ለማየት ይመኙት ነበር።
ከዚህ በፊት ቅዱሳን ነቢያት የተናገሩትን ቃልና በእናንተ ሐዋርያት አማካይነት ያገኛችሁትን የጌታችንንና የአዳኛችንን ትእዛዝ እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ።
እኔም ለመልአኩ ልሰግድለት በእግሩ ሥር በግንባሬ ተደፋሁ፤ እርሱ ግን “ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የኢየሱስን ምስክርነት ከያዙት ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ! የኢየሱስ ምስክርነት የትንቢት መንፈስ ነው” አለኝ።