እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርገህልናል፤ ከአንተ የሚወዳደር ማንም የለም፤ አንተ ለእኛ ያቀድክልንን መልካም ነገር ማንም ሊቈጥረው አይችልም፤ እኔ ስለ እነርሱ በዝርዝር ለመናገርና ለማውራት ብሞክር ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ይሆንብኛል።
ሉቃስ 1:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እኔ ከመጀመሪያው አንሥቼ ሁሉን ነገር በጥንቃቄ ከመረመርኩ በኋላ ታሪኩን በቅደም ተከተል እጽፍልህ ዘንድ መልካም ሆኖ አገኘሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክቡር ቴዎፍሎስ ሆይ፤ እኔም በበኩሌ ሁሉን ከመሠረቱ በጥንቃቄ ከመረመርሁ በኋላ፣ ታሪኩን ቅደም ተከተሉን በጠበቀ ሁኔታ ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመጀመሪያው አንሥቶ ስለሆኑት ነገሮች ሁሉ በጥንቃቄ በመመርመር፥ ለአንተ ቅደም ተከተሉን የጠበቀ ታሪክ ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው ተከትዬ፥ ሁሉንም በየተራው እውነተኛውን እጽፍልህ ዘንድ መልካም ሁኖ ታየኝ። |
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርገህልናል፤ ከአንተ የሚወዳደር ማንም የለም፤ አንተ ለእኛ ያቀድክልንን መልካም ነገር ማንም ሊቈጥረው አይችልም፤ እኔ ስለ እነርሱ በዝርዝር ለመናገርና ለማውራት ብሞክር ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ይሆንብኛል።
ስለዚህ በአንድነት ከተሰበሰብን በኋላ መልእክተኞችን መርጠን ከተወደዱት ወንድሞቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ ልንልካቸው ተስማማን።
ወንድማችን አጵሎስ ከሌሎች ወንድሞች ጋር እናንተን እንዲጐበኛችሁ በጥብቅ ለምኜው ነበር፤ ነገር ግን እርሱ አሁን ወደ እናንተ ለመምጣት አልፈቀደም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል።
ይህን ትምህርት ለአማኞች ብታስገነዝብ የእምነትን ቃልና የምትከተለውን መልካም ትምህርት እየተመገብክ ያደግኽ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።