ዘሌዋውያን 9:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም አንድ ወይፈንና አንድ የበግ ጠቦት ለአንድነት መሥዋዕት ያምጡ፤ እነዚህንም በዘይት ከታሸ የእህል መባ ጋር ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ፤ ዛሬ እግዚአብሔር ስለሚገለጥላቸው ይህን ሁሉ ያድርጉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኅብረት መሥዋዕት አንድ በሬና አንድ አውራ በግ በዘይት ከተለወሰ የእህል ቍርባን ጋራ በእግዚአብሔር ፊት ለመሠዋት አቅርቡ፤ እግዚአብሔር ዛሬ ይገለጥላችኋልና።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንድነትም መሥዋዕት በሬንና አውራን በግ፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቁርባን በጌታ ፊት ለመሠዋት ውሰዱ፥ ዛሬ ጌታ ተገልጦላችኋልና።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለደኅንነትም መሥዋዕት በሬንና አውራ በግን፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ፤ ዛሬ እግዚአብሔር ይገለጥላችኋልና ብለህ ንገራቸው።” |
እዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር ከወደ ምሥራቅ እየተገለጠ ነበር፤ ድምፁም እንደ ኀይለኛ የውሃ ማዕበል ነበር፤ የክብሩ ነጸብራቅም በምድር ላይ አበራ።
እነዚህ ቀኖች ካለፉ በኋላ ከስምንተኛው ቀን ጀምሮ ካህናቱ የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕታችሁን ያቀርባሉ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፤” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።
ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል፥ ምንም ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ጥጃና የአንድ ዓመት የበግ ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያመጡ ንገራቸው።
መላውም ማኅበር በድንጋይ ወግሮ ሊገድላቸው በእነርሱ ላይ ተነሣሣ፤ ነገር ግን በመገናኛው ድንኳን የእግዚአብሔር ክብር ለእስራኤላውያን ሁሉ ተገለጠ።
ከዚያም በኋላ ቆሬ መላውን ማኅበር በአንድነት ሰበሰበ፤ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ መጥተው በሙሴና በአሮን ፊት ለፊት ቆሙ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለመላው ማኅበር በድንገት ታየ።