Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 16:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከዚያም በኋላ ቆሬ መላውን ማኅበር በአንድነት ሰበሰበ፤ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ መጥተው በሙሴና በአሮን ፊት ለፊት ቆሙ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለመላው ማኅበር በድንገት ታየ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ቆሬም እነርሱን በመቃወም ተከታዮቹን ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በሰበሰባቸው ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ክብር ለመላው ማኅበር ተገለጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ቆሬም ማኅበሩን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእነርሱ ላይ ሰበሰበ፤ የጌታም ክብር ለማኅበሩ ሁሉ ተገለጠ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ቆሬም ማኅ​በ​ሩን ሁሉ ወደ ምስ​ክሩ ደጃፍ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሰበ​ሰበ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ተገ​ለጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ቆሬም ማኅበሩን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእነርሱ ላይ ሰበሰበ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለማኅበሩ ሁሉ ተገለጠ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 16:19
12 Referencias Cruzadas  

አሮንም ለመላው ማኅበር በተናገረ ጊዜ ፊታቸውን ወደ በረሓው አዞሩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር በደመና ተገለጠ፤


በማለዳ የእግዚአብሔርን ክብር ታያላችሁ፤ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ማጒረምረማችሁን ሰምቶአል፤ በእኛ ላይ የምታጒረመርሙት እኛ ማን ነን?”


ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ሕዝቡን ባረኩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ፤


ሙሴም “የእግዚአብሔር ክብር ስለሚገለጥላችሁ ይህን ሁሉ እንድታደርጉ እግዚአብሔር አዞአል።” አላቸው።


እግዚአብሔርም በደመና ዐምድ ወርዶ በድንኳኑ ደጃፍ በመቆም “አሮን! ማርያም!” ብሎ ጠራቸው፤ ሁለቱም ወደ ፊት ቀረቡ፤


መላውም ማኅበር በድንጋይ ወግሮ ሊገድላቸው በእነርሱ ላይ ተነሣሣ፤ ነገር ግን በመገናኛው ድንኳን የእግዚአብሔር ክብር ለእስራኤላውያን ሁሉ ተገለጠ።


ስለዚህም እያንዳንዳቸው ጥናቸውን ይዘው የእሳት ፍምና ዕጣን በመጨመር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ከሙሴና ከአሮን ጋር ቆሙ፤


እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤


ሙሴንና አሮንን ለመቃወም ሁሉም በአንድነት ከተሰበሰቡ በኋላ ወደ መገናኛው ድንኳን ዞር ብለው ሲመለከቱ ደመናው የመገናኛውን ድንኳን ሸፍኖት የእግዚአብሔር ክብር ተገለጠ።


በሰፈሩበት ቦታ ውሃ አልነበረም፤ ስለዚህ ሕዝቡ ሙሴንና አሮንን በመቃወም ተሰብስበው፥


ሙሴና አሮን ከሕዝቡ ፈቅ ብለው ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄዱ፤ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው ሳሉም የእግዚአብሔር ክብር ተገለጠላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos