Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 19:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በሦስተኛው ቀን በሕዝቡ ፊት በሲና ተራራ ላይ እኔ እግዚአብሔር ስለምወርድ ሁሉም በዚያ ቀን ይዘጋጁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በሦስተኛውም ቀን ይዘጋጁ፤ ምክንያቱም በዚያ ቀን በሕዝቡ ፊት እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በሦስተኛውም ቀን ይዘጋጁ፤ በሦስተኛው ቀን ሕዝቡ ሁሉ እያዩ ጌታ በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ይወ​ር​ዳ​ልና ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋ​ጅ​ተው ይጠ​ብቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በሦስተኛው ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና ለሦስተኛው ቀን ይዘጋጁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 19:11
20 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሰዎቹ ይሠሩአቸው የነበሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ፤


ወደ ሲና ተራራ ወርደህ ከሰማይ ሕዝብህን አነጋገርካቸው፤ ትክክለኛና ፍትሓዊ ሕግንና ሥርዓትን፥ መልካም የሆኑትን ደንቦችንና ትእዛዞችን ሰጠሃቸው።


እግዚአብሔር ሆይ! ሰማይን ሰንጥቀህ ውረድ፤ ተራራዎችን ዳስስ፤ እነርሱም ይጢሱ።


ሰማይን ሰንጥቆ ወደ ታች ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።


በሦስተኛው ቀን ማለዳ የነጐድጓድ ድምፅ አስተጋባ፤ የመብረቅ ብልጭልጭታና ጥቅጥቅ ያለ ደመና በተራራው ላይ ታየ፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የእምቢልታ ድምፅ ተሰማ። ሰዎቹም በሰፈሩበት ቦታ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።


እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት መላው የሲና ተራራ በጢስ ተሞላ። ጢሱም ከእሳት ምድጃ እንደሚወጣ ዐይነት ሆኖ ወደ አየር ተትጐለጐለ፤ ሰዎቹም እጅግ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።


እግዚአብሔር በሲና ተራራ ራስ ላይ ወርዶ፥ ወደ ተራራው ጫፍ እንዲመጣ ሙሴን ጠራው፤ ሙሴም ወደ ተራራው ጫፍ ወጣ፤


የእግዚአብሔርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ዐረፈ፤ ደመናውም ተራራውን ስድስት ቀን ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።


በተራራው ጫፍ ላይ የተገለጠው የእግዚአብሔር ክብር በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ እንደሚባላ እሳት ይታይ ነበር።


እነርሱንም ከግብጻውያን እጅ ለማዳን ወርጃለሁ፤ ከግብጽም አውጥቼ አሁን ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገችውን ሰፊና ለም የሆነችውን ምድር እሰጣቸዋለሁ።


ነገ ጠዋት ተዘጋጅተህ ከእኔ ጋር ለመገናኘት ወደ ሲና ተራራ ጫፍ ና።


እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ከእርሱ ጋር በዚያ ቆመ፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ብሎ ቅዱስ ስሙንም አስታወቀው።


እኔም ወደዚያ ወርጄ ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፤ ለአንተም ከሰጠሁህ መንፈስ ከፍዬ ለእነርሱ እሰጣቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ በእነዚህ ሕዝብ ላይ ያለህን ኀላፊነት በመሸከም ይረዱሃል፤ ከእንግዲህም ወዲህ ይህን ሁሉ ኀላፊነት ብቻህን አትሸከምም።


ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም።


እኔ ከሰማይ የወረድኩት የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ እንጂ የራሴን ፈቃድ ለማድረግ አይደለም።


ሙሴም እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጣ፤ ከኤዶም ላይ እንደ ንጋት ፀሐይ አበራ፤ ከፋራንም ተራራ ላይ አንጸባረቀ፤ በስተቀኙ የእሳት ነበልባል ነበር፤ ከእርሱም ጋር አእላፍ መላእክት ነበሩ።


እግዚአብሔር ‘ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ስለምፈልግ ሕዝቡን ሰብስብ’ ባለኝ ጊዜ በሲና ተራራ ላይ በእግዚአብሔር ፊት በቆማችሁበት ቀን ‘በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለእኔ እንዲታዘዙና፥ ልጆቻቸውም እኔን መፍራትን ያውቁ ዘንድ ያስተምሩአቸው’ ያለውን አስታውሱ።


ኢያሱም ሕዝቡን፦ “እግዚአብሔር ነገ በመካከላችሁ ተአምራትን ስለሚያደርግ ራሳችሁን አንጹ” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos