በኡሪምና በቱሚም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ የሚችል ካህን እስከሚነሣም ድረስ እነርሱ የተቀደሰውን ምግብ መብላት እንደማይችሉ ገዢው አዘዛቸው።
ዘሌዋውያን 8:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኤፉዱም ላይ የደረት ኪስ ሰፍቶ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚገለጥባቸውን ኡሪምና ቱሚምን አኖረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደረት ኪሱን በላዩ አደረገለት፤ በደረት ኪሱም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደረት ኪስ በእርሱ ላይ አደረገ፤ በደረቱ ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አኖረበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብሰ እንግድዓውንም በእርሱ ላይ አደረገ፤ በልብሰ እንግድዓውም ላይ የምልክትና የእውነት መገለጫዎችን አኖረበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደረት ኪስ በእርሱ ላይ አደረገ፤ በደረቱ ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አኖረበት። |
በኡሪምና በቱሚም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ የሚችል ካህን እስከሚነሣም ድረስ እነርሱ የተቀደሰውን ምግብ መብላት እንደማይችሉ ገዢው አዘዛቸው።
ስለዚህም የይሁዳ ገዥ በኡሪምና በቱሚም የሚያገለግል ካህን እስከሚነሣበት ጊዜ ድረስ ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ከሚቀርበው ቊርባን መመገብ የማይችሉ መሆናቸውን ነገራቸው።
“አሮንና ልጆቹ ካህናት ሆነው በፊቴ ያገለግሉኝ ዘንድ ለመለየት የምታደርገው ይህ ነው፤ ምንም ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት የበግ አውራዎችን ውሰድ፤
በዘለዓለማዊ ፍቅር በልብህ ውስጥ እንደ ማኅተም አትመኝ፤ በክንድህም እንደ ማኅተም እኔን ብቻ ያዘኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናት፤ ቅናትም እንደ መቃብር የከፋች ናት፤ የእሳትዋ ወላፈን እንደ እግዚአብሔር ወላፈን ነው።
ካህኑ አልዓዛር በኡሪም አማካይነት ፈቃዴን የሚያውቅ ስለ ሆነ ኢያሱ በአልዓዛር ይደገፋል፤ በዚህም ዐይነት አልዓዛር ኢያሱንና መላውን የእስራኤል ማኅበር በተግባር አፈጻጸማቸው ሁሉ ይመራቸዋል።”
ስለ ሌዊም ነገድ እንዲህ አለ፦ “ጌታ ሆይ! በቱሚምና በዑሪም አማካይነት በማሳና በመሪባ ውሃ ዘንድ ተከራክረህ ለፈተንካቸው ለአገልጋዮችህ ለሌዋውያን ፈቃድህን ግለጥ።
እኛ ግን የብርሃን ሰዎች ስለ ሆንን ራስን በመግዛት በመጠን እንኑር፤ እምነትንና ፍቅርን እንደ ጥሩር እንልበስ፤ የመዳንን ተስፋ እንደ ራስ ቊር እንልበስ፤
እርሱንም ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፥ እጣን እንዲያጥን፥ በፊቴ ኤፉድ እንዲለብስ፥ የእኔ ካህን ይሆን ዘንድ መረጥሁት፤ ለቀድሞ አባትህ ልጆችም የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡትን የሚቃጠል መሥዋዕት ሰጠኋቸው።
ስለዚህም ምን ማድረግ እንደሚገባው እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔር ግን በሕልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አማካይነት መልስ እንዲሰጠው አልፈቀደም።