ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ ሲያገለግሉ የሚለብሱአቸውን እጅግ የተዋቡትን የካህናት ልብሶች ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ሠሩ፤ የአሮንንም የክህነት ልብሶች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሠሩ።
ዘሌዋውያን 8:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ሕዝቡም ተሰበሰበ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ጌታ እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩንም ሁሉ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩ ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰቡ። |
ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ ሲያገለግሉ የሚለብሱአቸውን እጅግ የተዋቡትን የካህናት ልብሶች ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ሠሩ፤ የአሮንንም የክህነት ልብሶች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሠሩ።
እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በደረት ኪሱ ላይ ያሉትን ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ክር አሠሩ፤ በዚህ ዐይነት የደረት ኪሱ ከቀበቶው በላይ ስለሚውል በቀላሉ የማይፈታ ጥብቅ ነበር።
እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከወርቅ ክር፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና፥ ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ በብልኀት የተጠለፈው ቀበቶ አንድ ወጥ በመሆን ከኤፉዱ ጋር ተያይዞ ተሠራ።
እነርሱም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ነገድ በመወከል እንዲታሰቡ በትከሻ ላይ በሚወርዱት በኤፉዱ ጥብጣቦች ላይ አኖሩአቸው።
ቀጥሎም ሙሴ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት የአሮንን ወንዶች ልጆች ወደፊት አቅርቦ ቀሚስ አለበሳቸው፤ በወገባቸውም ዙሪያ መታጠቂያ አድርጎ በራሳቸውም ላይ ቆብ ደፋላቸው።
ቀጥሎም ሙሴ ፍርምባውን ወስዶ በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ አቀረበ፤ ስለ ክህነት ሹመት ከሚቀርበው የበግ አውራ የሙሴ ድርሻ ይህ ነበር።
ስለዚህም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ በመፈጸም ሰባት ቀን ሙሉ ሌሊትና ቀን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ትቈያላችሁ፤ ይህን ባታደርጉ ግን ትሞታላችሁ፤ ይህ እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሕግ ነው።”
በራሱም ላይ ጥምጥም አደረገለት፤ በጥምጥሙም ላይ ከፊት ለፊት በኩል እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በወርቅ አጊጦ የተሠራውን የቅድስና ምልክት የሆነውን አክሊል አኖረ።
እኔ የተቀበልኩትን በመጀመሪያ ደረጃ ያለውን ነገር ለእናንተ አስተላለፍኩላችሁ፤ ያስተላለፍኩላችሁም ነገር በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈው ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤