“አሮንና ልጆቹ ከሚካኑበት አውራ በግ ተወስዶ ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ። እርሱም ተመልሶ ለካህናቱ የሚመደብ ድርሻ ይሆናል።
ዘሌዋውያን 7:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአንድነቱ መሥዋዕት በቀኝ በኩል ያለው ወርች ድርሻው ሆኖ ለካህኑ ይሰጥ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኅብረት መሥዋዕታችሁን የቀኝ ወርች ለካህኑ የተለየ አድርጋችሁ ስጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰላም መሥዋዕታችሁ ቀኝ ወርቹን እንደ ቁርባን አድርጋችሁ ለካህኑ ትሰጡታላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከደኅንነት መሥዋዕታችሁ ቀኝ ወርቹን ለማንሣት ቍርባን እንዲሆን ለካህኑ ትሰጡታላቸሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከደኅንነት መሥዋዕታችሁ ቀኝ ወርቹን ለማንሣት ቁርባን እንዲሆን ለካህኑ ትሰጡታላችሁ። |
“አሮንና ልጆቹ ከሚካኑበት አውራ በግ ተወስዶ ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ። እርሱም ተመልሶ ለካህናቱ የሚመደብ ድርሻ ይሆናል።
ነገር ግን በመወዝወዝ ልዩ መባ ሆኖ ለእግዚአብሔር ከቀረበ በኋላ የካህናቱ ድርሻ እንዲሆን ስለ ተፈቀደ ፍርምባውንና ወርቹን አንተና ቤተሰብህ ሴቶች ልጆችህ ጭምር ትበሉታላችሁ፤ ይህንንም በተቀደሰ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤ ይህም የእስራኤል ሕዝብ የአንድነት መሥዋዕት አድርገው ከሚያቀርቡት መባ ሁሉ ተከፍሎ ለአንተና ለልጆችህ ተሰጥቶአል።
ከእስራኤላውያን የአንድነት መሥዋዕት መካከል የተወዘወዘውን ፍርንባና የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤላውያን እንደሚቀርብላቸው ቋሚ ድርሻ አድርጌ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ።
ከዚህም በኋላ ካህኑ ይህን ሁሉ ወስዶ ለእግዚአብሔር የሚወዘወዝ ልዩ መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤ ይህም ሁሉ የካህኑ ድርሻ ሆኖ ከሚነሣው ከአውራው በግ ፍርንባና ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል፤ ናዝራዊው የወይን ጠጅ መጠጣት የሚፈቀድለትም ከዚያን በኋላ ነው።
ስለዚህም የወጥቤቱ ሠራተኛ ምርጥ የሆነውን የታናሽ ብልት ሥጋ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠ፤ ሳሙኤልም ሳኦልን “ተመልከት፤ ይህ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ምርጥ ሥጋ ነው፤ እኔ ከጋበዝኳቸው እንግዶች ጋር ሆነህ እንድትበላ ያስቀመጡልህ ስለ ሆነ እርሱን ተመገብ” አለው። ስለዚህም በዚያ ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር አብሮ ተመገበ፤