ዘሌዋውያን 5:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው በፍርድ አደባባይ በይፋ ለምስክርነት መጥቶ ያየውን ወይም ስለ ጉዳዩ የሚያውቀውን ነገር ባይመሰክር ኃጢአት ይሆንበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘አንድ ሰው ስላየውና ስለሚያውቀው ነገር ሕጋዊ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ተጠይቆ ቃሉን ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆን፣ ይህ ሰው ኀጢአት ሠርቷልና ይጠየቅበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማንም ሰው የመሓላን ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ ወይም ስለ ነገሩ አይቶ ወይም አውቆ ባይናገር፥ ኃጢአት መሥራቱ ነውና በደሉን ይሸከማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንድ ሰው ቢበድል፥ የሚያምለውንም ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይናገር በደሉን ይሸከማል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም ሰው የሚያምለውን ቃል ቢሰማ፥ ምስክር ሆኖም አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ ወይም አውቆ እንደ ሆነ ባይናገር፥ ኃጢአት መሥራቱ ነውና በደሉን ይሸከማል። |
“አንድ ሰው ባልንጀራውን መበደሉን የሚገልጥ ክስ ቀርቦበት በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደሚገኘው መሠዊያ አምጥተውት ከበደል ንጹሕ መሆኑን በመሐላ በሚያረጋግጥበት ጊዜ፥
ያ ሰው የእግዚአብሔር አገልጋዮች ወደሆኑት ዳኞች ዘንድ ይሂድ፤ የሰውዬውን እንስሳ አለመስረቁንም በመሐላ ያረጋግጥ፤ እንስሳው ያልተሰረቀ ከሆነ የእንስሳው ባለቤት ካሳ አይጠይቅ፤ እንስሳው የጠፋበትም ሰው ካሳ አይክፈል።
ብዙ ሀብት ቢኖረኝ “እግዚአብሔር ማን ነው?” ብዬ አንተን እስከ መካድ እደርሳለሁ፤ ድኻ ብሆን ደግሞ እሰርቅ ይሆናል፤ በዚህም ሁኔታ የአንተን የአምላኬን ስም አሰድባለሁ።
ምድሪቱ እግዚአብሔርን በተዉ አመንዝሮች ተሞልታለች፤ ነቢያቱ ኀይላቸውን ያለ አግባቡ ይጠቀማሉ፤ የክፋትንም መንገድ ይከተላሉ፤ ከእግዚአብሔር ርግማን የተነሣ፥ ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ መስኮችም ደርቀዋል።
ሞት የሚገባው ኃጢአት ለሚሠራ ሰው ብቻ ነው፤ ልጅ ስለ አባቱ ኃጢአት አይቀጣም፤ አባትም ስለ ልጁ ኃጢአት አይቀጣም፤ ደግ ሰው በደግነቱ መልካም ዋጋውን ያገኛል፤ ክፉ ሰውም በክፋቱ ይቀጣል።
አንድ ሰው እኅቱን ወይም በአንድ በኩል ብቻ ከአባቱ ወይም ከእናቱ የተወለደችውን እኅቱን አግብቶ ፍትወታዊ ግንኙነት ቢያደርጉ ይህ አስነዋሪ ነገር በመሆኑ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ፤ ከእኅቱ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ስላደረገ ፍዳውን ይቀበላል።
“ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ማንም ሰው ተሳስቶ ኃጢአት ቢሠራ ወይም ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዱን ቢተላለፍ ከዚህ የሚከተለውን ሥርዓት ይጠብቅ፦
“አንድ ሰው ለእግዚአብሔር መክፈል የሚገባውን ባለመክፈል ሳያውቅ በደል ቢፈጽም፥ ለእግዚአብሔር የበደል መሥዋዕት የሚሆን ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ያምጣ፤ ወይም በቤተ መቅደሱ ሚዛን መሠረት ዋጋው ተገምግሞ ይክፈል። ይህም የበደል መሥዋዕት ነው።
ከተረፈው ሥጋ ምንም ያኽል በሦስተኛው ቀን ቢበላ የዚያን ሰው መሥዋዕት እግዚአብሔር አይቀበልለትም፤ መሥዋዕቱም እንደ ቀረበ ሆኖ አይቈጠርለትም፤ እንዲያውም እንደ ረከሰ ሆኖ ይቈጠራል፤ እርሱንም የበላ ሰው የበደሉን ፍዳ ይቀበላል።
ንጹሕ የሆነ እና ወደ ሩቅ አገር ያልሄደ ማንኛውም ሰው የፋሲካን በዓል በወቅቱ ባያከብር ከሕዝቤ ይለይ፤ መባውን በተወሰነው ጊዜ ባለማቅረቡ፥ ስለ ኃጢአቱ ተገቢውን ቅጣት ይቀበላል።
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። የካህናት አለቃውም እንደገና ኢየሱስን “በሕያው እግዚአብሔር ስም ይዤሃለሁ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ መሲሕ እንደ ሆንክ ንገረን!” አለው።
እርሱም አንድ ቀን እናቱን እንዲህ አላት፤ “አንድ ሰው አንድ ሺህ አንድ መቶ ጥሬ ብር በሰረቀሽ ጊዜ ያን የሰረቀሽን ሰው ስትረግሚው ሰምቼሽ ነበር፤ እነሆ ያ ብር በእኔ እጅ ነው፤ እርሱንም የወሰድኩ እኔ ነበርኩ።” እናቱም “ልጄ! እግዚአብሔር ይባርክህ!” አለችው።